
መጋቢት 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም ባንክ የአፍሪካ ዳይሬክተር ታውፊላ ንያማድዛቦ (ዶ.ር) ከገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ፣ ከፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ.ር)፣ ከጤና ሚኒሰትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ጋር የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው ድጋፍ ስለሚጠናከርበትና በባንኩ ድጋፍ እየተከናወኑ ባሉና ወደፊት ተፈጻሚነት ላይ በሚውሉ ፕሮጀክቶች ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል፡፡
ለባንኩ ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር በኢትዮጵያ ስላለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስለተሠሩ ስራዎች፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ለማዘመንና ለማሻሻል ስለተደረጉ ጥረቶች፣ የውጭ ባለሀብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስክ መሰማራት እንዲችሉ እየተሰጡ ስላሉ ድጋፎች፣ የግብርናው ዘርፍ ምርታማነትን ለማሳደግ በተለይም የመስኖ የስንዴ ልማትን ለማሳደግ እየተከናወኑ ስላሉ ጥረቶች ውይይት ተደርጓል፡፡
በኢትዮጵያ ያለውን የጸጥታ ችግር በሰላም ለመፍታት ስለሚደረጉ ጥረቶች፣ በጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸውና ለተፈናቀሉ ወገኖች እየተሰጠ ስላለው ሰብዓዊ እርዳታ፣ በጦርነት የወደሙ መሠረተ ልማቶች መልሶ የመገንባት ሂደት እንዲሁም ዘላቂ ሰላምንና ልማትን ለማረጋገጥ ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን ስለመቋቋሙ ጥልቅ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡
የባንኩ ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ከገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይትም የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ የልማት አጋር መኾኑን አመልክተዋል። ባንኩ ለመሠረተ ልማቶች ግንባታና ለመሠረታዊ አገልግሎቶች መስፋፋት ለሚሰጠው ድጋፍና ኢኮኖሚያዊ ትብብር ያላቸውን ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው ድጋፍ ሀገሪቱ በጦርነት፣ በድርቅና በኮሮናቫይረስ የደረሰባትን ጉዳት ለመቋቋም የላቀ አስተዋጽኦ እንዳለው አቶ አሕመድ መግለጻቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ከዓለም አቀፉ የልማት ድርጅት የሚገኘው ሀብት የትምህርት፣ የጤና፣ የግብርና፣ የመጠጥ ውኃና የመንገድ መሠረተ ልማቶችን ለማስፋፋትና ሀገሪቱ የነደፈችውን የ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ እውን ለማድረግ እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡
የዓለም ባንክ የአፍሪካ ዳይሬክትር ታውፊላ ንያማድዛቦ (ዶ.ር) በበኩላቸው ኢትዮጵያ በግጭት፣ በድርቅና በኮሮናቫይረስ ጉዳት ውስጥ አልፋ አሁንም በልማት ጎዳና ለመራመድ የምታደርገውን ጥረት መገንዘባቸውን አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ የዓለም ባንክ በልማት አጋርነቱ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
ዳይሬክተሩ ከመንግሥት ከፍተኛ ኀላፊዎች በተጨማሪም ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) እንዲሁም ከአፍሪካ ኅብረት ዋና ጸሐፊዎች ጋር የሸገር፣ የእንጦጦና የአንድነት ፓርክን ጎብኝተዋል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/