በባሕር ዳር ከተማ ግሽ ዓባይ ክፍለ ከተማ በሕገወጥ መንገድ የተከማቸ የምግብ ዘይትና ስኳር በቁጥጥር ስር ዋለ።

162

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ የግሽ ዓባይ ክፍለ ከተማ አሥተዳደር ከፀጥታ ኃይል ጋር በመቀናጀት በሕገወጥ መንገድ የመሠረታዊ ፍጆታ ምርቶችን ያከማቹ ነጋዴዎችን በመፈተሽና የዋጋ ተመን በማውጣት በሥርዓት እንዲያከፋፍሉ አሠራር ቢቀመጥም በመደበቅ እና ጨለማን ተገን በማድረግ ወደ ሌላ ቦታ የማዘዋወር ተግባር ሲፈጸም በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የ2ኛ ፖሊስ ዋና ጣቢያ አስታውቋል።
የጣቢያው የሙስና ወንጀል ምርመራ ክፍል ኀላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ፈለቀ ያለው በክፍለ ከተማው ንግድና የሰላም አስከባሪ ኃይል ጋር በተደረገ ክትትል በሌሊት ወደ ሌላ ቦታ ለማዘዋወር በመኪኖች የተጫነና ከአንድ ነጋዴ ማከማቻ በሕገወጥ መንገድ የተከዘነ በግምት ከ760 በላይ ጀሪካን ዘይት እና ከ600 ኩንታል በላይ ስኳር ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ገልጸዋል።
ሕግ የማስከበርና ገበያ የማረጋጋት ሥራ ወደፊትም የበለጠ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ ኅብረተሰቡ ሕገወጥነትን በመከላከልና ራሱንም ከዚህ ዓይነት ድርጊት በመጠበቅ መሥራት ይጠበቅበታል ነው ያሉት፡፡
የግሽ ዓባይ ክፍለ ከተማ አሥተዳደር ንግድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ገበይ የዋጋ ተመን በማውጣት ለተገዥ ያልኾኑትን የማሸግና በሕግ እንዲጠየቁ በማድረግ በኩል እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል፡፡
ችግሩን በዘላቂነት ፈትቶ ሰላምና መረጋጋት ያለበት የግብይት ሥርዓት መፍጠር ላይ አሁንም ችግር እያጋጠመ ነው ብለዋል። የሚፈለገው ለውጥ እንዲመጣ ኹሉም አካል የየድርሻውን ኀላፊነት እንዲወጣ ጥሪ ማቅረባቸውን ከባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር መንግሥት ኮምዩኒኬሽን የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበአሸባው የትግራይ ወራሪ ቡድን ከፍተኛ ዘረፋና ውድመት የደረሰበት የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሙሉ በሙሉ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተገልጿል፡፡
Next articleየኢትዮጵያ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ በልማት አጋርነቱ እንደሚቀጥል የዓለም ባንክ ገለጸ።