በአሸባው የትግራይ ወራሪ ቡድን ከፍተኛ ዘረፋና ውድመት የደረሰበት የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሙሉ በሙሉ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተገልጿል፡፡

107

ደሴ: መጋቢት 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባው የትግራይ ወራሪ ቡድን በደሴ ከተማ በወረራ በቆየባቸው ጊዜያት የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ላይ ከፍተኛ ዘረፋና ውድመት አድርሷል፡፡ ሆኖም ወራሪ ቡድኑ ከአካባቢው ከለቀቀ በኋላ በኅብረተሰቡ፣ በመንግሥት ተቋማትና በአጋር ድርጅቶች ከፍተኛ ርብርብ አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ ሃይማኖት አየለ (ዶ.ር) ገልጸዋል፡፡
ሥራ አስኪያጇ በቀጣይም ወደ ሆስፒታሉ ለሚመጡ ተገልጋዮች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እየተሠራ እንደኾነ አስረድተዋል፡፡ ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ጋር በመተባበርም የኩላሊት እጥበት ህክምና በቅርቡ ለመስጠት መታሰቡን ዶክተር ሃይማኖት ተናግረዋል፡፡
የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በህልውና ዘመቻው ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ከፌዴራል ጤና ሚኒስቴር እውቅና የተሰጠው ሲሆን ይህም የሕዝቡና የሰራተኛው ውጤት መሆኑን ነው ሥራ አስኪያጇ የጠቀሱት፡፡
የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር ትብብር ላደረጉ ሁሉ ሆስፒታሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡
ዘጋቢ፡- ተመስገን አሰፋ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበኩር ጋዜጣ መጋቢት 12/2014 ዓ.ም ዕትም
Next articleበባሕር ዳር ከተማ ግሽ ዓባይ ክፍለ ከተማ በሕገወጥ መንገድ የተከማቸ የምግብ ዘይትና ስኳር በቁጥጥር ስር ዋለ።