
መጋቢት 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በመላው አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የዳያስፖራ ወገኖች በአሜሪካ ምክር ቤቶች በኢትዮጵያ ላይ ለማሳለፍ የታቀዱት እጅግ አደገኛ ረቂቅ ሕጎች እንዳይጸድቁ ከፍተኛ ዘመቻ እንዲያደርጉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡ።
አቶ ደመቀ በመላው አሜሪካ ከሚገኙ የኮሚዩኒቲ አደረጃጀት ኀላፊዎች፣ የታስክ ፎርስ፣ የሲቪክ ማኅበራት አመራሮችና ተወካዮች ጋር በበይነ መረብ ውይይት አድርገዋል።
በአሜሪካ ኮንግረስ እና ሴኔት በኩል በረቂቅ ደረጃ የሚገኙት ኤች አር 6600 እንዲሁም ኤስ 3199 በሚል የቀረቡ ረቂቅ ሕጎች ኢትዮጵያውያን በደም መስዋእትነት ያስከበሩትን ሉዓላዊነት በእጅ አዙር ለመቀማት የተሸረቡ ሴራዎች ናቸው ብለዋል።
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የኅብረተሰብ ክፍል ጨምሮ ዳያስፖራውን ከእናት ሀገሩ እና ቤተሰቦቹ ጋር የሚያቆራርጥ እጅግ አሳሪ እና ታይቶ የማይታወቅ የሉዓላዊነት መቀሚያ ረቂቅ ሕጎች ናቸውም ነው ያሉት።
ባለፈው አንድ ዓመት ተኩል ኢትዮጵያ ገጥሟት የነበረውን ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ጫና ለመቋቋም ዳያስፖራው ቁር እና ፀሐይ ሳይበግረው ላሳየው እውነተኛ ሀገር ወዳድነት ምሥጋና አቅርበዋል፡፡ እነዚህ ረቂቅ ሕጎችም እንዳይጸድቁ ከምንጊዜውም በላይ በተቀናጀ የአንደነት ዘመቻ እንዲንቀሳቀሱ ጠይቀዋል።
መንግሥት እየወሰዳቸው የሚገኙ እርምጃዎች ሀገርን ያስቀደሙ እና ዘላቂ ሰላምና አንድነትን ታሳቢ በማድረግ የሚወሰኑ መኾናቸውን ጠቁመው በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ መቼም ቢኾን እንደማይደራደር ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያለትን ረጀም ዘመን ያስቆጠረ ግንኙነት እንዲጠናከር ኹሌም ዝግጁ መኾኗን የገለጹት አቶ ደመቀ ሉዓላዊነቷን የሚጋፉ የእጅ አዙር ጥምዘዛ እንደማትቀበል ነው ያረጋገጡት።
አምባሳደር ፍጹም አረጋ በበኩላቸው ዳያስፖራው በየአካባቢው ያሉ የመንግሥት ተመራጮችን በስልክ፣ በኢሜል፣ ፊርማ በማሰባሰብና በአካል እያገኘ የረቂቅ ሕጎቹን አፍራሽነት እንዲያስረዳ ጥሪ አቅርበዋል።
በውይይቱ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎችም ረቂቅ ሕጎቹ የመንግሥትና የፓርቲ ሳይኾኑ የሀገርን አንድነትና ቀጣይነት አደጋ ላይ የሚጥሉ በመኾናቸው ከምንጊዜውም በላይ በቅንጅት በመሥራት ባሉበት እንዲመክኑ እንደሚሠሩ ቃል መግባታቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
