በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ እየተከናወነ ባለው የበጋ መስኖ ልማት ከ57 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዶ እየተሠራ ነው፡፡

137

ባሕር ዳር: መጋቢት 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በምራብ ጎጃም ዞን በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ 1ሺህ 142 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ እየለማ ነው።

በወረዳው እየለማ ያለውን የበጋ መስኖ ስንዴ ከክልል፣ ከዞንና ከወረዳ የተውጣቱ የሥራ ኀላፊዎች፣ ስንዴን በመስኖ ያለሙ እና በቀጣይ ለማልማት የተዘጋጁ አርሶ አደሮች ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ የአማራ ክልል ግብረና ቢሮ ኀላፊ ልዩ አማካሪ እና የኤቲኤ አስተባባሪ ተስፋሁን መንግሥቴ በበጋ መስኖ እየለማ ያለው የመስኖ ስንዴ ኢኮኖሚው ላይ እየገጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ድርሻው ከፍተኛ ነው ብለዋል። በሥራው ለተሳተፉ አርሶ አደሮችም ምስጋና አቅርበዋል።

አርሶ አደሮቹ የበጋ መስኖ ስንዴን ለማምረት በርካታ ውጣውረድ ቢኖረውም ምርታማ በመኾናቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ የግብዓት አቅርቦት ችግር እና የነዳጅ እጥረት እንዲፈታላቸውም ጠይቀዋል።

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ተስፋዬ ሽፈራው (ዶ.ር) ባዩት ነገር መደሰታቸውንና በቀጣይ ዩኒቨርስቲው ሥራውን የበለጠ ለማገዝ እንደሚሠራ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ዩኒቨርስቲው የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ገዝቶ እያቀረበ መኾኑንም ተናግረዋል።

በምራብ ጎጃም ዞን በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ እየተከናወነ ባለው የበጋ መስኖ ሥራ 57 ሺህ 100 ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዶ እየተሠራ እንደኾነ ከወረዳው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር ለአማራ ክልል የውኃ መሳቢያ ፓምፖችን ድጋፍ አደረገ።
Next articleዳያስፖራው ኤች አር 6600ና ኤስ 3199 የተባሉት አደገኛ ረቂቅ ሕጎች እንዳይጸድቁ በተቀናጀ የአንደነት ዘመቻ እንዲንቀሳቀስ አቶ ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡ፡፡