የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር ለአማራ ክልል የውኃ መሳቢያ ፓምፖችን ድጋፍ አደረገ።

680

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር ቆላማ አካባቢዎችን ለማልማት ከአማራ ክልል መስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ጋር እየሠራ ነው፡፡ ለዚሁ ተግባር የሚውሉ 10 የውኃ መሳቢያ ፓምፖችንም ለክልሉ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ ድጋፉን ባስረከቡበት ጊዜ እንዳሉት የሀገሪቱን ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ ቆላማ አካባቢዎችን ትኩረት ሰጥቶ ማልማት አስፈላጊ ነው፡፡ ሚኒስትሯ የተደረገው ድጋፍም አርሶ አደሮችን ከችግር ለማውጣት አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል መስኖ እና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ኀላፊ ዶክተር ኢንጅነር ዳኝነት ፈንታ ሚኒስቴሩ ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

የውኃ ፓምፖቹ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ለሚገኙ ቆላማ ወረዳዎች እንደሚሰራጩ አስረድተዋል፡፡

ክልሉ ለመስኖ ልማት ከፍተኛ አቅም እንዳለው ያስረዱት ኀላፊው በቀጣይ በክልሉ ያልተጠናቀቁ የመስኖ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ትኩረት እንደሚሰጥም በወቅቱ ተናግረዋል።

በጅምር የቀሩ እና ያልተጠናቀቁ የመስኖ ፕሮጀክቶች የመልካም አሥተዳደር እና የሕዝብ ቅሬታ ምንጭ እየኾኑ በመምጣታቸው በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ ይሠራልም ነው ያሉት፡፡

ዘጋቢ፡- ሰለሞን ዘመኑ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየአሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን አጀንዳ ሕዝቡ ከሠራዊቱ ጋር በመኾን ሊያከሽፍ እንደሚገባ ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ አሳሰቡ።
Next articleበባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ እየተከናወነ ባለው የበጋ መስኖ ልማት ከ57 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዶ እየተሠራ ነው፡፡