
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ተረክሂን ከባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሣኅሉ (ዶ.ር) በከተማ እድገት፣ በመሰረተ ልማቶችና በከተሞች ትስስር ዙሪያ በባሕር ዳር መክረዋል፡፡
አምባሳደሩ ባሕር ዳር ከተማን ለእህት ከተማነት እንደሚመርጧት በውይይታቸው ተናግረዋል፡፡
የባሕር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሣኅሉ (ዶ.ር) ከተማዋ የእምቅ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት መኾኗን ለአምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡ ከተማዋ ለጉብኝት ተመራጭ መኾኗንም አብራርተዋል፡፡
በውይይቱ ኹለቱ ከተሞች በከተማ ልማትና ተያያዥ ጉዳዮች በጋራ ለመሥራት መምከራቸውን ከባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/