የሕዝብን ጥያቄ የእኔ ነው በማለት መናገርና ለመፈፀም መትጋት እንደሚገባ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬ አሳሰቡ።

98

ባሕር ዳር: መጋቢት 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ለአማራ ክልል ምክር ቤት አባላት በተልዕኳቸው ዙሪያ በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ የሚመክር መድረክ በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።

በምክክር መድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬ የምክክር መድረኩ ዓላማ ሥራችንን ስናከናውን የምናወጣውን ሕግ ለመፈፀምና የምክር ቤቱ አሠራሮችን ከሕግ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ምን እንዲሚመስል ለመገንዘብ ነው ብለዋል።

የምክር ቤቱ አባላት እርስ በርሳቸው በመተዋወቅ የጋራ ጥያቄ እንዲኖር ለማድረግም ያስችላል ብለዋል። ባሕልና እሴትን በሚያዳብር መልኩ መተዋወቅና መግባባት ለሥራው ውጤታማነት አስፈላጊ መኾኑንም ተናግረዋል። እርስ በርስ መተዋወቅ ጥያቄዎችን የጋራ በማድረግ ለመፍታት እንደሚያስችልም ገልጸዋል።

የምክክር መድረኩ የምክር ቤት አባላት ውክልናቸውን በተገቢው መንገድ ለመፈፀም የሚያስችሉ ጉዳዮችን የሚቀስሙት እንደሚኾንም ተናግረዋል።

ውክልናን ለመወጣት ሕብረት ወሳኝ መኾኑንም አንስተዋል። ስለ ክልሉ ለመነጋገር እና የመፍትሔ ሐሳብ ለማመንጨት መግባባት ግድ እንደሚልም ጠቅሰዋል። ሐሳብን በነፃነት በመግለፅ የዴሞክራሲ ልምምድን ማስፋፋት እንደሚገባም አሳስበዋል። የአመለካከትና የተግባር አንድነት ያለው ሕዝብ ለመፍጠር ግንኙነትን ማዳበር እንደሚገባም ገልጸዋል። ውክልናን በብቃት ለመወጣት ዋጋ መክፈል ግድ እንደሚልም ተናግረዋል። የሕዝብን ጥያቄ የእኔ ነው በማለት መናገርና ለመፈፀም መትጋት እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት።

የሕዝብ ተወካዮች የሕዝብን ሐሳብ በተገቢው መንገድ ማቅረብ እንደሚገባቸውም ገልጸዋል። ሕዝቡ ሊፈታለት ከሚፈልጋቸው ጥያቄዎች ላይ በማተኮር ከስሜታዊነት በመፅዳት ሐሳብን ማራመድ እንደሚገባም ተናግረዋል። የሚቀርቡ ጥያቄዎች ስሜታዊነትን ያስወገዱ፣ የሕዝብን ጥቅም የሚያስከብሩና ጥርጣሬን የማይፈጥሩ መኾን እንዳለባቸውም ገልጸዋል።

“እኛ የምንወክለው ታላቁን የአማራ ሕዝብ በመኾኑ ሐሳባችንን በሚገባ መሸጥ ይገባናል” ነው ያሉት።

የአማራ ሕዝብና የአማራ ክልል ምክር ቤት በርካታ ጥያቄዎች እንዳሉት የገለፁት አፈ ጉባዔዋ የሌሎችን ሐሳብ በመግዛት በሰከነ መንገድ ሐሳባችን በመሸጥ ጥያቄዎችን መመለስና ማስመለስ ይገባልም ብለዋል።

የአማራ ሕዝብ ትልልቅ ችግሮችን ለመፍታት መሠረት እየጣልን እና ሐሳብን እየሸጠን መሄድ አለብንም ነው ያሉት። በሐሳቦቻችን የሌሎችን ቀልብ ስበን የሕዝባችን ጥቅም ማረጋጋጥ አለብንም ብለዋል። ንትርክ ውስጥ መግባት የሕዝብን ጥያቄ እንደማያስመለስ ገልጸዋል። የሕዝብን ችግር በውል ለይተን መተጋል አለብንም ብለዋል። የምክክር መድረኩ የሕዝብ ውክልናውን በአግባቡ ለመወጣት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ማተኮር ይገባልም ነው ያሉት።

የምክር ቤቱ አባላት ሕግ የማውጣት፣ ክትትልና ቁጥጥር የማድረግና ውክልናን በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችል ገንቢ ሐሳቦችን በምክክር መድረኩ ያገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል ።

ለአማራ ክልል ምክር ቤት አባላት በተልዕኳቸው ዙሪያ የሚመክረው መድረክ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይወያያል ነው የተባለው።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ወራሪውን ቡድን እስካልደመሰስን ድረስ እንቅልፍ አይወስደንም” የጠገዴ ወረዳ ሚሊሻዎች
Next articleየቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናን ኢትዮጵያ ከዓለም አንደኛ በመሆን አጠናቀቀች።