
ባሕር ዳር: መጋቢት 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ዶክተር በለጠ ሞላን በድጋሚ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል።
አቶ መልካሙ ሹምዬ ደግሞ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።
አብን ለሦስት ቀናት ሲያካሂድ በቆየው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባው የሥራ አስፈፃሚ አባላቱን በአዲስ በማደራጀት ማጠናቀቁን የፖርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ጣሂር መሐመድ ገልጸዋል።
በዚህም መሠረት፦
ዶክተር በለጠ ሞላ – ሊቀመንበር
መልካሙ ሹምዬ – ምክትል ሊቀመንበር
ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ – የውጭ ግንኙነት ኃላፊ
ዩሱፍ ኢብራሒም – የሕግ ጉዳዮች ኃላፊ
ክርስቲያን ታደለ – የፖሊሲ እና ስትራቴጂ ክፍል ኃላፊ
ጋሻው መርሻ – የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ
ጣሂር መሐመድ – የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
ዶክተር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም – የአብን ጽህፈት ቤት ኃላፊ
ሐሳቡ ተስፋየ – አደረጃጀት ጉዳዮች ኃላፊ አድርጎ የሥራ አስፈፃሚውን በአዲስ አደራጅቷል።
ከተመረጡት የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚዎች መካከል 3ቱ አዲስ መሆናቸው ተገልጿል።
ፖርቲው በዛሬው ዕለትም 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በባህር ዳር ማካሄድ ጀምሯል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/