
መጋቢት 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) መማክርት ጉባዔው የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ይፋ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ያሉ ጉዳዮችን በአንክሮ እየተከታተለ እንደኾነ ገልጿል።
የአማራ ክልል 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ውጤት ከዚህ ቀደም ይመዘገብ ከነበረው ያነሰ መኾኑን መረጃ ማግኘቱንም አስታውቋል።
ይህንን መሠረት በማድረግም የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባዔ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ዝቅተኛ ውጤት እንዲመዘገብ ያጋጠሙ ምክንያቶችን ለማጣራት ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር በቅርበት እየሠራ እንደሆነ የጽሕፈት ቤቱ ኀላፊ ዶክተር ዳዊት መኮንን ገልጸዋል።
መረጃና ማስረጃን ምክንያት በማድረግ የውጤት መቀነስ ሥረ መሠረታዊ ምክንያቱን በትክክል ለማወቅ ኹሉንአቀፍ ጥረት እያደረገ እንደኾነም ጠቅሰዋል።
ባልተለመደ መልኩ የአማራ ክልል ተማሪዎች ውጤት መቀነስ ጉባዔውን እንዳሳሰበው የገለጹት ዶክተር ዳዊት የችግሩን ምክንያት ከማወቅ ጀምሮ መፍትሔ እንዲሰጠው የሚጠበቅበትን ሚና ይጫወታል ነው ያሉት። ለዚህም ከፈተና እና ምዘና ባለሙያዎች፣ ከሶፍትዌር ባለሙያዎች እና ከመምህራን ጋር እየመከረ መኾኑን አመላክተዋል።
ዘጋቢ:- ደጀኔ በቀለ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/