ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ኦክስፋም በኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን የሰብዓዊ ድጋፍ አደነቁ።

155

መጋቢት 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የኦክስፋም ኢንተርናሽናል ዋና ዳይሬክተር ጋብሪኤላ ቡቸርን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይቱ ድርቅ፣ ኮሮናቫይረስ፣ ግጭት እና መፈናቀል በኢትዮጵያ በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎችን ሕይወት አደጋ ላይ መጣሉ የተነሳ ሲኾን ከኦክስፋም እና ከሌሎች የሰብዓዊ አጋሮች ሁለገብ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

አቶ ደመቀ እንዳሉት ፥ በአንዳንድ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በድርቅ የተጎዱ ዜጎችን ለመደገፍ ኦክስፋምን ጨምሮ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር መንግሥት ጥረት እያደረገ ነው።

በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ወደ 23 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አንስተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን በመንግሥት በኩል እየተወሰዱ ስላሉ አበረታች እርምጃዎች ገለጻ አድርገዋል። ይህም መንግሥት በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት ጠቅሰዋል።

ኦክስፋም በኢትዮጵያ የሚያደርገውን ሰብዓዊ ድጋፍ አድንቀው ፥ ድርጅቱ በሀገሪቱ እያከናወነ ያለውን እንቅስቃሴ እንደሚደግፉ ቃል ገብተዋል።

የኦክስፋም ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው ፥ ድርጅታቸው በኢትዮጵያ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ የሚደርሱ ችግሮች የበርካታ ሰዎች ሕይወት ላይ የሚያደርሱትን ተጽዕኖ እንደሚገነዘቡ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ችግር ለመቅረፍም ድርጅታቸው አስፈላጊውን ኹሉ ድጋፍ እንደሚያደርግም መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

በውይይቱ በኢትዮጵያ የኦክስፋም ዳይሬክተር፣ በአፍሪካ ቀንድ፣ ምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ በኦክስፋም የቀጣናው የፕሮግራሞች ኀላፊ እና የአፍሪካ ሕብረት የኦክስፋም ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተሳትፈዋል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ርስት አልባ ባለ ርስቶች፣ ባለ ጸጋ ችግረኞች”
Next article‹‹የተማሪዎች ውጤት መቀነስ እኛን ስለሚመለከት ችግሩ እስኪፈታ ቢሮው እስከመጨረሻ ይቀጥላል›› ዶክተር ማተብ ታፈረ