የደሴ ዙሪያ ወረዳ አሥተዳደር አሸባሪውን የትግራይ ቡድን ለመደምሰስ በተካሄደው የኅልውና ዘመቻ በጀግንነት ተጋድሎ ለፈጸሙ የጸጥታ ኀይሎች እውቅና ሰጠ።

164

ደሴ: መጋቢት 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን አማራን በማጥፋት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ያደረገው እኩይ ሙከራው እንዲከሽፍ ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚሊሻ ጎን ተሰልፈው ጀብድ የፈጸሙ የደሴ ዙሪያ ወረዳ የጸጥታ ኀይሎች በወረዳው አሥተዳደር እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በመርኃ ግብሩ ላይ የተገኙት የደሴ ዙሪያ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ አቶ መሐመድ ሰይድ እንዳሉት የወረዳው የጸጥታ ኀይሎች ከወገን ጥምር ጦር ጎን ተሰልፈው አኩሪ ተጋድሎ በመፈጸም ኀላፊነታቸውን በብቃት ተወጥተዋል ብለዋል።
የተሰጣቸው እውቅና ለቀጣይ ተልዕኮ የሚያዘጋጅ መኾኑን ተሸላሚ የጸጥታ ኀይል አባላት ገልጸዋል።
በእውቅና መርኃ ግብሩ ላይ የቀድሞው የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ሰይድ መሐመድ፣ የሃይማኖት አባቶችና የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ:- አሊ ይመር
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከተፈተኑት 11 ሺህ 953 ተማሪዎች ዉስጥ ወደ ዩኒቨርሲቲ ያለፉት 3 ሺህ 42 ተማሪዎች ብቻ ናቸዉ።
Next article“ርስት አልባ ባለ ርስቶች፣ ባለ ጸጋ ችግረኞች”