
ደብረ ብርሃን: መጋቢት 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በ2013 ዓ.ም በሁለት ዙር ከተፈተኑት 11 ሺህ 953 ተማሪዎች ዉስጥ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያመጡት 3 ሺህ 42 ተማሪዎች ብቻ ናቸዉ።
የሰሜን ሸዋ ዞን ትምህርት መምሪያ
ምክትል ኃላፊ ወሰን ለገሰ ዞኑ በፀጥታ ስጋት ችግር ዉስጥ ሆኖ ነዉ ተማሪዎችን አስፈትኖ የነበረዉ ብለዋል፡፡
ችግር የነበረባቸዉ አካባቢዎች ላይ የተፈተኑ ተማሪዎች ከሌሎች ጋር እኩል የማለፊያ ነጥብ ወጥቶ መመዘናቸዉ የፈተና ሂደቱን ችግር እንደሚያሳይም ገልጸዋል፡፡
“ጉዳዩ ትኩረት የሚያስፈልገዉ ስለነበር ቀደም ብለን በየደረጃዉ እነዚህ ተማሪዎች ልዩ ትኩረት እንዲሰጣቸዉ ስንጠይቅ ብንቆይም የማለፊያ ነጥቡ የፀጥታ ችግር በሌለባቸዉ አካባቢዎች ከተፈተኑት ተማሪዎች እኩል ሆኗል” ብለዋል፡፡
አሁንም ቢሆን ይህ ጉዳይ መፍትሔ እንዲሰጠው አስገንዝበዋል፡፡
ዘጋቢ:– ዮሐንስ ንጉስ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/