የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን የተሟላ የገንዘበና የቴክኒክ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ።

82

መጋቢት 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን የተሟላ የገንዘበና የቴክኒክ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ፡፡
የዩኒሴፍ የምሥራቅና የደቡብ አፍሪካ ቀጣናዊ ቢሮ የሕጻናት ጥበቃ አማካሪ አንድሪው በሮክስ ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ.ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡
ዶክተር ኤርጎጌ እንደገለጹት መንግሥት በጦርነቱ እና በድርቅ ምክንያት የተጎዱ አካባቢዎችንና በዚሁ ምክንያት የተፈናቀሉ የኅብረተሰብ ክፍሎችን፣ ሴቶችንና ሕጻናትን የመደገፍና የማቋቋም ሥራን እየሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከዩኒሴፍ ጋር ለረጅም ጊዜያት የቆየና በተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የኹለትዮሽ ግንኙነት እንዳላት ገልጸው ይህንንም ለማጠናከር እንዲቻል በሚኒስቴሩና በድርጅቱ በኩል የሚከናወኑ ማኅበራዊ ድጋፎችን አቀናጅቶ ለተጎጂዎች ተደራሽ በማድረግ ትክክለኛ ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የዩኒሴፍ የምሥራቅና የደቡብ አፍሪካ ቀጣናዊ ቢሮ የሕጻናት ጥበቃ አማካሪ አንድሪው በሮክስ የተፈናቀሉ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በአማራ ክልል መመልከታቸውንና በጦርነቱ ምክንያት የተፈጠረው ማኅበራዊ ችግር ከባድ መኾኑን ገልጸዋል።
በተለይም በክልሉ ጦርነቱ በሴቶችና ሕጻናት ላይ ያስከተለው ጉዳት ከፍተኛ እንደኾነ ነው ያመላከቱት፡፡
በጦርነቱና በድርቁ ምክንያት የተጎዱ አካባቢዎችንና የኅብረተሰብ ከፍሎችን ለመደገፍና ከዚህ በፊት ከነበረው የላቀ የተሟላ የድጋፍ አገልግሎትና ቅንጅታዊ ሥራዎች በድርጅቱና በመንግሥት በኩል ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ዩኒሴፍ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በርካታ ዘርፈ ብዙ የማኅበራዊ ድጋፎችን እያከናወነ ይገኛል።
በቀጣይም በግጭቱና በድርቁ ምክንያት የተጎዱ አካባቢዎችን የመደገፍ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ፣ ለሕጻናት የአልሚ ምግብ ድጋፍ የማድረግ፣ በሕጻናት ድጋፍና ጥበቃ ዙሪያ ተዓማኒ መረጃ እንዲኖር የተደራጀ ሥርዐት የመፍጠር፣ በችግር ውስጥ የሚገኙ ሕጻናትን መደገፍና ሌሎች ተግባራትን እንደሚያከናውን ተመላክቷል።
ሚኒስትሯ የድርጅቱን ለረጅም ጊዜ የቆየ ያልቶቀጠበ ድጋፍና ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የኹለትዮሽ ግንኙነት አድንቀዋል።
በቀጣይም ድርጅቱ ያለውን ከፍተኛ የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፍ በተለይም በጦርነትና በድርቅ ምክንያት የተጎዱ አካባቢዎችን ለመደገፍና የረጅም ጊዜ የጋራ ዓላማን ለማሳካት እንዲቻል ድርጅቱ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“በተማሪዎች ውጤት እና መቁረጫ ነጥብ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርበናል” የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
Next articleመንግሥት የኢትዮ ቴሌኮምን የ40 በመቶ ድርሻ ወደ ግል የማዛወር ሂደት አራዘመ።