“በተማሪዎች ውጤት እና መቁረጫ ነጥብ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርበናል” የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

788

መጋቢት 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አስመልክቶ መረጃ መረጃ አጋርቷል።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሁለቱም ዙር በሰላማዊ መንገድ እንዲሰጥ የሚፈለግብንን ሁሉ አድርገናል ብሏል።
የአንደኛው ዙር ፈተና እንደተጠናቀቀ ለሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት በወቅቱ ፈተና ተሰርቋል እየተባለ በማኅበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ በነበረው የተለያየ መረጃ ምክንያት የፈተና ውጤት ትንተናው በጥንቃቄ እንዲታይ በጽሑፍ ጥያቄ ማቅረቡን ገልጿል።
ውጤት ከተገለፀ በኋላም የቀረቡ ቅሬታዎችን መሠረት በማድረግ ፈተናቸው ድጋሜ እንዲታይላቸው የጠየቁ ተማሪዎችን ውጤታቸው እንዲፈተሽላቸው ሁኔታዎችን ከማመቻቸት በተጨማሪ አጠቃላይ በውጤቱ እና መቁረጫ ነጥቡ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርበናል ነው ያለው ቢሮው።
ትምህርት ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንደሚሰጥ ዛሬ ገልጾልናል ነው ያለው ቢሮው።
በሚኒስቴሩ በኩል አስፈላጊው ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ በትምህርት ቢሮው በኩል የሚፈለጉ መረጃዎች ካሉ ከሕዝቡ የሚደብቀው መረጃ እንደማይኖር ትምህርት ቢሮ ገልጿል።
የተማሪዎች ውጤት ለዞኖች፣ ወረዳዎች እና ትምህርት ቤቶች በግልፅ የተላለፈ ስለኾነ ለመሸፋፈን የሚፈልግ አካልም የለም፤ መሸፋፈንም አይቻልም ብሏል ትምህርት ቢሮ።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየዋግ ተፈናቃይ አርሶ አደሮች ወደ ቀያቸው ተመልሰው እንዲያርሱ ትኩረት እንዲሰጥ ተጠየቀ፡፡
Next articleየተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን የተሟላ የገንዘበና የቴክኒክ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ።