
ባሕር ዳር: መጋቢት 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን ማዕከላዊ ኮሚቴ ዛሬ የድርጅቱን መደበኛ ስብሰባ በባሕር ዳር ማካሄድ ጀምሯል። የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ጣሂር መሐመድ ስብሰባውን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ያለፉት ጊዜያት የፓርቲው እንቅስቃሴ ይዳሰሳል፤ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችም እንደሚቀመጡ አስታውቀዋል።
የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊው በሀገሪቱ ተለዋዋጭ የፖለቲካ ሁኔታ ምክንያት የአማራ ሕዝብ አሁንም ለከፋ ችግር እየተጋለጠ ነው ብለዋል።
በማዕከላዊ ኮሚቴው ስብሰባውም በወቅታዊው የፖለቲካ ሁኔታ አብን ለሕዝቡ ሊያበረክት ስለሚችለው አስተዋጽኦ፣ በቅርቡ በሚደረገው የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባዔ ቅድመ ዝግጅት ላይ፣ ስድስተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ምን ይመስል እንደነበር እና በሂደቱ የአብን ሚና ምን ይመስል እንደነበር በስፋት ተነስቶ ጥልቅ ውይይት ይደረግበታል ነው ያሉት።
አቶ ጣሂር እንዳሉት በሀገሪቱ የተፈጠረውን ጦርነት በመቀልበስ ሂደቱ የአብን ድርሻ እንዴት እንደነበር በስፋት ይፈተሻል። የሕልውና ዘመቻው የተመራበት ሀገራዊ ሁኔታን በመገምገም ቀጣይ ሊከናወኑ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይም ይመክራል ተብሏል።
ሁሉን አቀፍ እና አካታች ሀገራዊ መግባባትን በተመለከተ አብን በተለይ የአማራ ሕዝብን ተጠቃሚ ማድረግ የሚችልባቸውን ጉዳዮችም ይዳስሳል ነው ያሉት።
ማዕከላዊ ኮሚቴው የድርጅቱን የቀጣይ አምስት ዓመታት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅም ይጠበቃል።
በዚህ ውይይት ሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታ በስፋት የሚተነተን ሲሆን የድርጅቱን የአሠራር ሥርዓቶች በመከተል በኩል መስተካከል ያለባቸውን ክፍተቶች በሚመለከትም ይመክራል ተብሏል። የማዕከላዊ ኮሚቴው ውይይት ለሁለት ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
ዘጋቢ:- ደጀኔ በቀለ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/