
ወልድያ: መጋቢት 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ካስፈተኑ 42 ትምህርት ቤቶች በስድስት ትምህርት ቤቶች የተፈተኑ 679 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አላመጡም፡፡
ጊራና ፣ ቃሊም፣ ኩል መሰክ፣ ጉርጉር ደብረሮሀ፣ ሀናመኳት ደብረሲና እና ክበበው 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መኾናቸው ተገልጿል፡፡
የሰሜን ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ባለሙያ ወይዘሮ ሙሉ አዳነ ዞኑ ከ5 ወራት በላይ ጦርነት ሲካሄድበት በመቆየቱና አሁንም ቀጣናው ሙሉ በሙሉ ሰላሙ ባልተረጋገጠበት ተማሪዎች ለፈተና በቂ ዝግጅት ሳያገኙ ፈተና መውሰዳቸውን አስረድተዋል፡፡
በጦርነቱ ምክንያት ከደረሰው ሥነ ልቦና ጉዳት ሳያገግሙ ተማሪዎች ፈተና መውሰዳቸው ተገቢ አለመኾኑን የገለጹት ወይዘሮ ሙሉ ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ የወሰነው ማለፊያ ነጥብ ይኸንን ግምት ውስጥ ያላስገባ ነው ብለዋል፡፡
👉በዞኑ 9 ሺህ 710 ተማሪዎች ተፈትነው 3 ሺህ 657 ተማሪዎች ብቻ ናቸው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ማለፊያ ነጥብ ያመጡት።
ዘጋቢ:- ባለ ዓለምዬ -ከወልድያ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/