የአማራ ክልል ምክር ቤት ከመጋቢት 15 ጀምሮ መደበኛ ጉባዔውን እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

509

ባሕር ዳር: መጋቢት 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት ከመጋቢት 15/2014 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ ጉባዔውን እንደሚያካሂድ የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬ አስታውቀዋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ ምክር ቤቱ ስለሚያደረግው መደበኛ ጉባኤ መግለጫ ሰጥተዋል።

ምክር ቤቱ ስድስተኛ ዙር አንደኛ ዓመት ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔውን ነው የሚያካሂደው። ምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤው የስድስት ወር የሥራ አፈፃፀም ይገመግማል ነው የተባለው። ጉባዔው መጋቢት 15 -16/2014ዓ.ም በክልል ምክር ቤት ያደርጋል።

ምክር ቤቱ በሚኖረው መደበኛ ጉባዔ የስድሰተኛው አንደኛ መደበኛ ጉባዔን ቃለ ጉባዔ ያፀድቃል። የበጀት ዓመቱን የስድስት ወር የመልካም አሥተዳደርና የልማት እቅድ የሥራ አፈፃፀም ይገመግማል ነው ያሉት።

ክልሉ በስድስት ወር ፈታኝ ወቅት ማሳለፉን ያስታወሱት አፈ ጉባዔዋ የፀጥታ ጉዳይና የልማት ሥራዎች በጉባዔው ሪፖርት እንደሚቀርብ ነው የተናገሩት። ክልሉ በፈታኝ ወቅት ቢኾንም የተሠሩ መልካም ሥራዎች መኖራቸውንም አንስተዋል።

የመጀመሪያው ጉባዔ ሲያካሂድ በርካታ የክልሉ አካባቢዎች በጠላት ተይዘው እንደነበር አስታውሰዋል። አሁን ላይም የተያዙ አካባቢዎች ቢኖሩም ጠላት ከአብዛኛው የክልሉ አካባቢ መውጣቱን ነው የገለፁት። በክልሉ አንፃራዊ ሰላም እንደሚገኝ ተናግረዋል። ነፃ የወጡ አካባቢዎች መልሶ የማልማት እንቅስቃሴ እየተካሄደም መኾኑንም ተናግረዋል። ምክር ቤቱ በመልሶ ግንባታ ላይም ውይይት ካደረገ በኋላ የቀጣይ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥም አፈ ጉባዔዋ አስታውቀዋል።

ጉባዔው የቋሚ ሰብሳቢዎችን ጨምሮ ልዩ ልዩ ሹመቶችን እንደሚያፀድቅም አስታውቀዋል።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“መንግሥት የዜጎችን ጥቃት ለማስቆም ጠንካራ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ሊኖረው ይገባል”
Next article“በዞኑ 6 ትምህርት ቤቶች የተፈተኑ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አላመጡም” የሰሜን ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ