
አዲስ አበባ: መጋቢት 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር ዶክተር መሰንበት አሰፋ በሀገሪቱ እየተስተዋሉ ያሉ ማንነትን መሰረት ያደረጉ ብሔር ተኮር ጥቃቶችን ፈጥኖ ማስቆም ካልተቻለ ሀገሪቱን ወደ ከፋ ችግር ሊያስገባት እንደሚችል አስገንዝበዋል።
ጥቃቶችን በዘላቂነት ለማስቆምም ብሔራዊ ምክክሩን በአግባቡ መጠቀም የተሻለ መፍትሔ ያመጣል ብለዋል። ዶክተር መሰንበት ብሔራዊ ምክክሩ ሀገርን በማዳንና በማሻገር ጠንካራ ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሚያስችል መሰረት የሚጣልበት መድረክ እንዲሆንም መንግሥት፣ ምሁራንና ፖለቲከኞች ሰፊ ኀላፊነት አለባቸው ነው ያሉት።
ፖለቲከኞች የግል ፍላጎታቸውን ወደ ጎን በመተው የሕዝብ ጥያቄና ፍላጎት ላይ ብቻ መሰረት በማድረግ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ሰላምን፣ አንድነትን፣ ልማትንና እድገትን ሊያመጣ በሚያስችል መሰረት ላይ በመቆም ምክክሩን ትርጉም ባለው መልኩ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ገልጸዋል።
ዶክተር መሰንበት “ሀገራችን ያለችበትን አስቸጋሪ ጊዜ ለመሻገር የፖለቲካ ብስለትና ቁርጠኝነት ይጠይቃል፤ በተለይም መንግሥት የዜጎችን መፈናቀልና ግድያ ከመቃወም ባለፈ ለማስቆም በቁርጠኝነት ሊሠራ ይገባል፤ የዜጎችን በየትኛውም ቦታ የመኖር መብትን በማረጋገጥ ደኅንነታቸውን ሊያስጠብቅ ይገባል” ብለዋል።
ዘጋቢ:- ስነ-ጊዮርጊስ ከበደ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/