በዋግ ኽምራ ለዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ከወሰዱ 2 ሺህ 923 ተማሪዎች ውስጥ 2 ሺህ 218ቱ የማለፊያ ውጤት ማምጣት አለመቻላቸውን የአሥተዳደሩ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።

227

መጋቢት 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ዓመቱን ሙሉ በትግራይ ወራሪ ኃይል ምክንያት በመፈናቀል፣ በአሌክትሪክ ኃይል እጥረት ያለፕላዝማ እና መደበኛ ትምህርት እየተቆራረጠ ይሰጥ የነበረው ትምህርት በተማሪዎች ውጤት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ አሳርፏል።
የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰይፉ ሞገስ ለአሚኮ እንዳስታወቁት
👉በብሔረሰብ አሥተዳደሩ ከሚገኙ 16 መሰናዶ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 15ቱ ተማሪዎችን ያስፈተኑ ሲኾን በጠቅላላ ከተፈተኑት 2 ሺህ 923 ተማሪዎች ውስጥ 705ቱ ብቻ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ሲኾን 2 ሺህ 218 የሚኾኑት ደግሞ የማለፍያ ውጤት ማምጣት እንዳይችሉ የጦርነቱ ዳፋ በተማሪዎች ሕይወት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳርፏል ብለዋል።
በአሥተዳደሩ
👉በተፈጥሮ ሳይንስ 1 ሺህ 107 ተፈትነው 369ኙ ወይንም (33%) ያለፉ ሲኾን
👉በማኀበራዊ ሳይንስ ደግሞ 1 ሺህ 816 ተማሪዎች ለፈተና ተቀምጠው 336ቱ ወይንም (18 ነጥብ 5%) ማለፊያ አግኝተዋል።
👉በብሔረሰብ አስተዳደሩ ለፈተና ከተቀመጡ 1 ሺህ 636 ሴት ተማሪዎች መካከል ደግሞ 380 (23.2%) ብቻ ማለፊያ ውጤት አምጥተዋል።
👉ፈተና ከሰጡ 15 ትምህርት ቤቶች መካከል በሦስት ትምህርት ቤቶች በመሪ፣ በሚሲግ እና ቅዳሚት ትምህርት ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ ያላለፈባቸው ሲኾን በሰርካለም ትዕዛዙ ትምህርት ቤት ደግሞ አንድ ተማሪ ብቻ ማሳለፍ መቻሉን ኀላፊው አስታውቀዋል።
የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰይፉ አኹንም ድረስ ዋግ ነጻ ባልወጣችበት እና የጦርነት ድምጾች በሚሰማበት አካባቢ ባልተረጋጋ መንፈስ የተፈተኑ ተማሪዎችን ታሳቢ ያደረገ የማለፍያ ነጥብ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲወስንላቸው ጠይቀዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር እንደሀገር ዋጋ እየከፈሉ ያሉ አካባቢዎች ላይ ያሉ ተፈታኞችን በልዮ ኹኔታ እንድያይ የሕዝቡ ከፍተኛ ጥያቄ ነው ያሉት ኀላፊው ማስተካከያ በማድረግ ለተፈታኞች መልካም የውድድር መንፈስ በመፍጠር የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ:- ግርማ ተጫነ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleውጤት ማምጣት አለመቻላቸውን የአሥተዳደሩ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።
Next article“መንግሥት የዜጎችን ጥቃት ለማስቆም ጠንካራ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ሊኖረው ይገባል”