በአግሮ ኢንዱስትሪ የፈጠራ ሐሳብ ውድድር አሽናፊዎች ተሸለሙ።

129

መጋቢት 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር እና ተባባሪ አካላት ሲካሄድ የቆየው ውድድር የግብርና ውጤቶችን በኢንዱስትሪ ማዘመንን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ንጉሡ ጥላሁን በግብርና ዘርፍ የአርሶ አደሩን ሕይወት ለማቃለል ያለመ የፈጠራ ሐሳብ ውድድር መካሄዱን አድንቀዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የቀለም ብቻ ሳይኾኑ ዕውቀት እና አመለካከት የሚቀረጽባቸው ናቸው ያሉት አቶ ንጉሡ የወጣቶቹ ሐሳብ ወደሥራ እንዲያድግ በማሰልጠን እና በመደገፍ ላይ ያሉትን እንደሚያበረታቱ ገልጸዋል። “ኢትዮጵያ ሐሳቦች ተወዳድረው የሚያሸንፉባት እንድኾሆን ተባብረን መሥራት አለብን” ነው ያሉት።

አቶ ንጉሡ ለውድድሩ አሸናፊዎች ሽልማት አበርክተዋል።

በውድድሩ ያሸነፉ እያንዳንዳቸው 230 ሺህ ብር የሥራ ማስጀመሪያ ገንዘብ እና ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

አሸናፊ የኾኑት የአግሮ ኢንዱስትሪ የፈጠራ ሐሳቦች ከተረፈ ምርት ማዳበሪያ ያመረቱ፣ ከቀርከሃ ብስክሌት የሠሩ፣ የእንስሳት መኖ ከተረፈ ምርቶች ያዘጋጁ፣ ከቡና ቅጠል በዘመናዊ መልክ ሻይ ቅጠል ያመረቱ እና ከእንሰት ስታርች እና የተለያዩ ምግቦችን ያቀረቡ መኾናቸውን ከሥራና እና ክህሎት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየዓለም የጤና ድርጅት የሕክምና ቁሳቁስ ወደ ትግራይ ክልል እንዳላደርስ በመንግሥት ተከልክያለሁ ማለቱ ከእውነት የራቀ መኾኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ፡፡
Next articleውጤት ማምጣት አለመቻላቸውን የአሥተዳደሩ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።