
መጋቢት 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም የድርጅቱን መርሆችና እሴቶች የጣሰ አካሄድ እየተከተሉ መኾኑንም የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል፡፡
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር በስዊዘርላንድ ጀኔቭ ትናንት በሰጡት መግለጫ “መንግሥት ወደ ትግራይ ክልል የሕክምና ቁሳቁስ እንዳይገባ ከልክሏል” በማለት የሐሰት መረጃ ሰጥተዋል።
“በትግራይ ክልል የሚኖሩ በርካታ ዜጎች የሕክምና አገልግሎት እንዳያገኙ ኾነዋል” በማለትም ተናግረዋል።
ኾኖም ዋና ዳይሬክተሩ የሰጡት መግለጫ ከእውነታው የራቀ እና መንግሥትን በሐሰትና ባልተገባ መልኩ የወነጀለ መኾኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ ገልጸዋል።
የአሸባሪው ሕወሓት ታጣቂዎች በአፋር ክልል ወረራ በመፈጸምና መንገድ በመዝጋት የሕክምና ቁሳቁስና ሌሎች እርዳታዎች ወደ ትግራይ እንዳይደርስ እያደረጉ መኾኑ እየታወቀ ዋና ዳይሬክተሩ መንግሥትን ተወቃሽ ማድረጋቸው ትክክል አለመኾኑን ተናግረዋል።
አሸባሪው ሕወሓት የእርዳታ መተላለፊያ ኮሪደሮችን መዝጋቱን ተከትሎ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አውሮፕላኖች በሳምንት ከሦስት ጊዜ በላይ ወደ ትግራይ እርዳታ እየተጓጓዘ መኾኑን ገልጸዋል፡፡
በመኾኑም የዓለም የጤና ድርጅትን ጨምሮ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ወደ ትግራይ ክልል የሕክምና ቁሳቁስ እንዳይደርስ እያደረገ ያለው አሸባሪው ሕወሓት መኾኑን በትክክል መገንዘብ አለባቸው ነው ያሉት ሚኒስትሩ።
ከዚህ አኳያ የዓለም የጤና ድርጅት አሸባሪውን ሕወሓት በግልጽ ሊያወግዝ እንደሚገባ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
“የዓለም የጤና ድርጅት በኢትዮጵያ በጦርነቱ የተጎዱ ኹሉንም አካባቢዎችን በፍትሐዊነት ከማገልገል ይልቅ ስለ አንድ አካባቢ ብቻ ትኩረት ሲያደርግ ይስተዋላል፤ ይህም ከድርጅቱ መርሆ አንፃር ትክክል አይደለም” ሲሉ ገልጸዋል።
በተለይ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ኾነ ብለው የተሳሳተ መረጃ እያሰራጩ መኾኑን ጠቅሰው መንግሥት ወደ ትግራይ ክልል የሕክምና ቁሳቁስ እንዳይገባ እንደከለከለ አድርገው መናገራቸው ፍጹም ከእውነት የራቀ መኾኑን ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ ቀደም የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የድርጀቱን መርሆችና እሴቶችን በጣሰ መልኩ ኃላፊነት የጎደለው አካሄድ እየተከተሉ መኾኑን በመግለጽ ቅሬታ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/