የኢትዮጵያ ባሕር ኀይል የተማረ እና በሥነምግባር የታነፀ የሰው ኀይል ለማፍራት እየሠራ መሆኑን ገለጸ፡፡

170

መጋቢት 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ባሕር ኀይሉ በባሕር ዳር ቅርንጫፍ በመጀመሪያ ዙር የተለያዩ የትምህርት ዓይነቶችን የተከታተሉ መሠረታዊ ባሕረኞችን አስመርቋል፡፡
የኢትዮጵያ ባሕር ኀይል ዋና አዛዥ ሬር አድሚራል ክንዱ ገዙ “ሰልጣኞች ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ የመጀመሪያውን የስልጠና ደረጃ አጠናቃችሁ ወደ ኹለተኛ ዙር በመድረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል፡፡
መከላከያ የሰለጠነ፣ በሥነ ምግባር የታነጸ እና ሀገሩን የሚድ የሰው ኀይል ለማፍራት በትኩረት በመሥራት ላይ መኾኑን የጠቀሱት ዋና አዛዡ ሰልጣኞች በቀጣይ የሚሰጣቸውን ስልጠና በመከታተል የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ለዓለም የሚያስተዋውቅ መርከበኛ ለመኾን እንዲሠሩ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ ባሕር ኀይል መሰረታዊ ባህረኛ ስልጠና አስተባባሪ ሻምበል ቡስሬ ቡልጉ በበኩላቸው ባሕር ኀይል እንደ አንድ የመከላከያ ተቋም ሊሰነዘሩ የሚችሉ ጥቃቶችን በመከላከል የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ስልጠናው መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

ባሕር ኀይሉን ለማዘመን በባሕር ዳር እና ቢሾፍቱ ቅርንጫፎችን ከፍቶ ስልጠና እየሰጠ ሲኾን ሰልጣኞች በቆይታቸው መሰረታዊ የቀለም ትምህርት፣ ወታደራዊ የመሳሪያ ትውውቅ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስልጠና መውሰዳቸውን አስተባባሪው ተናግረዋል፡፡
ከመሠረታዊ ባህረኛ ሰልጣኞች መካከል አስተያየታቸውን የሰጡት መሰረታዊ ወታደር ሮቤል ሙሉጌታ እና እንየው ብርሃን ስልጠናው ሕዝብ እና መንግሥት የሰጠንን ኀላፊነት በብቃት ለመወጣት ዕውቀት ያገኘንበት ነው ብለዋል፡፡
መረጃውን ያደረሰን በኢፊዴሪ አየር ኀይል የምዕራብ አየር ምድብ ጠቅላይ መምሪያ ነው፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየሰዎች ለሰዎች ግብረሰናይ ድርጅት እና ተስፋ ለኢትዮጵያ ከ4 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የሕክምና ቁሳቁስ ለደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድጋፍ አደረጉ።
Next articleየዓለም የጤና ድርጅት የሕክምና ቁሳቁስ ወደ ትግራይ ክልል እንዳላደርስ በመንግሥት ተከልክያለሁ ማለቱ ከእውነት የራቀ መኾኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ፡፡