የሰዎች ለሰዎች ግብረሰናይ ድርጅት እና ተስፋ ለኢትዮጵያ ከ4 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የሕክምና ቁሳቁስ ለደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድጋፍ አደረጉ።

193

ደሴ: መጋቢት 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው እና ወራሪው የትግራይ ቡድን ከፍተኛ ዘረፋ እና ውድመት ካደረሰባቸው ተቋማት መካከል አንዱ የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነው።
ሆስፒታሉ ከዚህ ቀደም የነበሩት የሕክምና መሳሪያ ቁሳቁስ በአሸባሪ ቡድኑ በመዘረፋቸው በርካቶች በሕክምና እጥረት ለእንግልት እና ለከፍተኛ ወጭ ተዳርገዋል።
የሰዎች ለሰዎች ግብረሰናይ ድርጅት የሀገር ውስጥ ምክትል ተጠሪ ዶክተር አስናቀ ወርቁ ድርጀቱ ከዚህ ቀደም መሰል ድጋፍ ማድረጉን አውስተው ግምታቸው 4 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የቀዶ ጥገና ሕክምና መስጫ ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።
በተመሳሳይ በአሜሪካ ኒውዮርክ እና ኒውጀርሲ አካባቢ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የተቋቋመው ተስፋ ለኢትዮጵያ ድርጅት ለሆስፒታሉ ድጋፍ አድርጓል።
የድርጅቱ ጸሓፊ ወሰንየለሽ እሸቱ ከ500 ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው የመድኃኒት ማቀዝቀዣ መሳሪያ ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል።
የደሴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ሃይማኖት አየለ ወራሪ ቡድኑ ባደረሰው ዘረፋ እና ውድመት ምክንያት የቀዶ ጥገና ሕክምና መስጠት ባለመቻሉ ከ1 ሺህ 500 በላይ ሰዎች ሕክምናው የሚጀመርበትን ጊዜ በመጠባበቅ ላይ ናቸው ብለዋል። የተደረገው ድጋፍም ይህን ችግር ይቃልላል ነው ያሉት።
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኀላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ በበኩላቸዉ አሸባሪው እና ወራሪው የትግራይ ቡድን በርካታ የጤና ተቋማት ላይ ዘረፋ እና ውድመት ማድረሱን አውስተው ተቋማቱን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ውስጥ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን አመሥግነዋል።
ዘጋቢ:- አንዋር አባቢ – ከደሴ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleቤተክርስቲያኗ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዐተ-ጸሎትና ቀብር በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምሥጋና አቀረበች።
Next articleየኢትዮጵያ ባሕር ኀይል የተማረ እና በሥነምግባር የታነፀ የሰው ኀይል ለማፍራት እየሠራ መሆኑን ገለጸ፡፡