
አዲስ አበባ: መጋቢት 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ወቅታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
ለአዳዲስ አምባሳደሮች የሀገራት ምደባ መሰጠቱን በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።
አምባሳደሮቹ የተመደቡባቸው ሀገራትም፡-
1. አምባሳደር ተፈራ ደርበው – ጃፓን
2. አምባሳደር ደሴ ዳልኬ – ደቡብ ኮሪያ
3. አምባሳደር ዶ/ር ስለሺ በቀለ- አሜሪካ
4. አምባሳደር ባጫ ደበሌ – ኬንያ
5. አምባሳደር ሀሰን ኢብራሂም – ግብፅ
6. አምባሳደር ዳባ ደበሌ -ሩዋንዳ
7. አምባሳደር ጀማል በከር – ፖኪሲታን
8. አምባሳደር ፈይሰል አሊይ – ኳታር
9. አምባሳደር ኢሳያስ ጎታ – ሞሮኮ
10. አምባሳደር ፀጋአብ ክበበው – አውስትራሊያ
11. አምባሳደር ምህረተአብ ሙሉጌታ – ስዊዲን
12. አምባሳደር ፍቃዱ በየነ – ኤርትራ
ተቀማጭነታቸው በኢትዮጵያ ኾኖ በተለያዩ ሀገሮች የተሾሙ አምባሳደሮች፦
13. አምባሳደር ጣፋ ቱሉ – ብራዚል
14. አምባሳደር ዶ/ር ገነት ተሾመ – ኩባ
15. አምባሳደር ሽታዬ ምናለ – ኮትዲቯር
16. አምባሳደር ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ – ኢንዶኔዥያ
17. አምባሳደር ረሻድ መሀመድ – ዝምባብዌ
በቆንስል ጅነራልነት የተመደቡ:
18. አምባሳደር አንተነህ ታሪኩን – ገዳሪፍ
19. አምባሳደር አክሊሉ ከበደ – ዱባይ
20. አምባሳደር ሰይድ መሐመድ – ሀርጌሳ
21. አምባሳደር አወል ወግሪስ – ባህሬን
በምክትል የሚሲዮን መሪነት፦
22. አምባሳደር አሳየ ዓለማየሁ – ጋና
23. አምባሳደር ኃይላይ ብርሃነ – ጀርመን
24. አምባሳደር ብዙነሽ መሠረት – ህንድ
25. አምባሳደር ዮሴፍ ካሳዬ – ኒው ዮርክ
26. አምባሳደር ዘላለም ብርሃን – ዋሽንግተን
27. አምባሳደር ፍርቱና ዲባኮ – ቤልጅየም
28. አምባሳደር ወርቃለማሁ ደሰታ- ኬንያ
29. አምባሳደር ውብሸት ደምሴ – እንግሊዝ
30. አምባሳደር ሙሉጌታ ከሊል- ፓኪስታን
በሌላ በኩል በሳምንቱ የአፍሪካ ቀንድ የቻይና ልዩ መልዕክተኛ በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጋቸውን አምባሳደር ዲና አንስተዋል። በጉብኝቱም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከልዩ መልዕክተኛው ጋር ምክክር ያደረጉ ሲኾን ቻይና ኢትዮጵያን በሚመለከት በፀጥታው ምክር ቤት ላሳየችው ድጋፍ ምሥጋና አቅርበውላቸዋል ነው ያሉት።
በሳምንቱ የኢትዮ- ቻይና ጉባዔ በበይነ መረብ ተካሂዷል። በጉባዔው ቻይና በኢትዮጵያ ውስጥ መሠረተ ልማቶችን በመገንባትና የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚደረገውን ድጋፍ እንደምታሳድግ ተገልጿል።
በሳዑዲ አረቢያ እስካሁን 35 ሺህ ኢትዮጵያውያን ወደሀገራችው ለመመለስ መመዝገባቸውን አምባሳደር ዲና ገልጸዋል።
በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ በጦርነት የወደሙ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት 110 ሺህ ራንድ አሰባስበው መላካቸውንም አምባሳደሩ በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።
ዘጋቢ:- አንዱዓለም መናን- ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/