የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ባለፉት ስድስት ወራት በርካታ የጦር መሳሪያዎችንና የገንዘብ ኖቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።

133

አዲስ አበባ: መጋቢት 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ኮማንደር ፋሲካ አሰፋ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ በተሠራው ሥራ ለሽብር ተግባር ሊውሉ የነበሩ በአይነት የሚለያዩ በርካታ የጦር መሳሪያዎችንና የገንዘብ ኖቶችን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል።
በከተማዋ በተደረገ ፍተሻና ብርበራም 47 ቦምብ፣ 8 ፈንጂዎች፣ 113 ክላሽን ኮቭ ጠብመንጃ ፣ 422 ልዩ ልዩ ሽጉጦች ከ17 ሺህ በላይ የክላሽን፣ ከ8ሺ በላይ የሽጉጥ ጥይቶች፣ 2ሺህ 901 የብሬን፣ 8 የመትረየስ እና 183 የልዩ ልዩ የጦር መሳሪያ ጥይቶች መያዝ ተችሏል ብለዋል ኮማንደር ፋሲካ።
ከእነዚህ የጦር መሳሪያዎች በተጫማሪ 57 የጦር መሳሪያ መነፅር፣ 2 የጦር መሳሪያ ኮምፓስ፣ 64 ወታደራዊ የመገናኛ ሬድዮ፣ 3 የመገናኛ ሬዲዩ ቻርጀር፣ 6 ጂፒኤስ እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁስ ከእነ ተጠርጣሪዎቹ ተይዘው አስፈላጊው ምርመራ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡
የሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዘውውርን ለመከላከል ሕገወጦችን ሕግ ፊት የማቅረቡ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስረድተዋል።
ከሐምሌ 30/2014 ዓ.ም እስከ ታኅሣሥ 30/2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ በከተማው ልዩ ልዩ ሥፍራዎች 18 ፈንጂዎች፣ 50 ቦምብ፣ 1ሺህ 544 የብሬን እና የዲሽቃ ጥይቶች፣ 21 ክላሽን ኮቭ ጠብመንጃዎች፣ 16 ሽጉጦች፣ 20 የመገናኛ ሬዲዮኖች፣ 11 የጦር ሜዳ መነፅር፣ ከ2ሺ በላይ ልዩ ልዩ የፀጥታ አካላት የደንብ ልብሶች እና ሌሎች ቁሳቁስ ተጥለው ተገኝተዋልብም ተብሏል።
ኮሚሽኑ በከተማዋ ካሉ የተለያዩ የሰላምና ደኅንነት ተቋማት ጋር በጥምረት እየሠራ መሆኑንም አስታውቋል።
ዘጋቢ፡-እንዳልካቸው አባቡ -ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleኢትዮጵያ የ2022ቱን “ዓለም አቀፍ የኢኖቬሽን አፍሪካ ዲጂታል ጉባኤን” ልታስተናግድ ነው።
Next articleዜና መጽሔት ባሕር ዳር: መጋቢት 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ)