
መጋቢት 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የ2022ቱን ዓለም አቀፍ የኢኖቬሽን አፍሪካ ዲጂታል ጉባኤ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኮምዩኒኬሽን ባለስልጣን እና ኤክስቴሽያ በትብብር የሚያዘጋጁት ነው።
በጉባኤው ከ30 በላይ ሀገራት የተውጣጡ ከ300-500 የሚደርሱ ሚኒስትሮች፣ የቴክኖሎጂ ድርጅት ኃላፊዎች እና ከፍተኛ የኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ይሳተፋሉ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ.ር) የኢኖቬሽን ዲጂታል አፍሪካ ጉባኤ በኢትዮጵያ እንዲካሄድ መደረጉ ኢትዮጵያ ተመራጭ እየኾነች መምጣቷን ማሳያ ነው ብለዋል።
ጉባኤውን ለማስተናገድ የኢትዮጵያን ዝግጁነት ያረጋገጡት ሚኒስትሩ ጉባኤው ኢትዮጵያ ለያዘችው የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ አጋዥ የኾኑ የመፍትሔ ሐሳቦችን የምታገኝበት እንደሚኾን መግለጻቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ጉባኤው ግንቦት 3 እና 4/2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲኾን ለፖሊሲ አውጪዎች፣ በዘርፉ ለተሰማሩ ድርጅቶችና ግለሰቦች የዲጂታል ቴክኖሎጂ የመፍትሔ ሐሳቦች የሚቀርቡበት ይኾናል ተብሎ ይጠበቃል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/