
ባሕር ዳር: መጋቢት 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
ዶክተር ይልቃል ውይይቱን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ምክክሩ በአማራ ክልል አሁናዊ የሰላምና ደኅንነት ጉዳይ፣ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በከፈተው ጦርነት እና ሰብዓዊ ድጋፍ በሚደረግባቸው ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ነው፡፡
በውይይቱ ርእሰ መሥተዳድሩ የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ ለአምባሳደሯ ገለጻ አድርገዋል፡፡ የአማራ ሕዝብ ሰላም ፈላጊ፣ ኹሉንም ነገር በሥርዓት የሚፈታ ሕዝብ መኾኑንም ገልጸዋል፡፡
አሸባሪው ቡድን ወደ ትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይደርስ መንገድ በመዝጋት ሕዝቡን ለርሃብ እንዳጋለጠው አስገንዝበናል ብለዋል። ይህም የትግራይ ሕዝብ ከአሸባሪው ቡድን ውጪ አማራጭ የሌለው ለማስመሰል እየተጠቀመበት መኾኑን ነው ርእሰ መሥተዳድሩ ገለጻ ያደረጉት፡፡ በዚህም ኃላፊነቱን መውሰድ ያለበት ራሱ አሸባሪው ቡድን እንደኾነ አስረድተዋል፡፡
በውይይቱ በቂ ግንዛቤ እንደተፈጠረ ያነሱት ርእሰ መሥተዳድሩ በቀጣይ በጋራ መሥራት የሚቻልበት ሰፊ እድል መኖሩን አምባሳደሯ ተገንዝበዋል ነው ያሉት፡፡
“አሜሪካ በአማራ ክልል የምታደርገው ሰብዓዊ ድጋፍ እና መልሶ ግንባታ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል” ብለዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ በአማራ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ጋር ፍሬያማ ውይይት መደረጉንም ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/