ኢትዮጵያ እና ቻይና ስትራቴጂካዊ የትብብር አጋርነታቸውን እንደሚያጠናክሩ ገለጹ።

201

መጋቢት 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የቻይና የውጭ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ዴንግ ሊ ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱም በኢትዮ- ቻይና የኹለትዮሽ ፖለቲካ ምክክር ላይ ያተኮረ ነው፤ ለኹለተኛ ጊዜ ነው የተካሄደው።
በበይነ መረብ በተካሄደው ውይይትም በኹለትዮሽ፣ ክልላዊ እና በባለብዙ ወገን የጋራ ጉዳዮች ላይ ሐሳብ ተለዋውጠዋል። በቀጣይም ኹሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ የትብብር አጋርነታቸውን ለማጠናከር ከመግባባት ላይ ደርሰዋል።
አምባሳደር ሬድዋን ቻይና በፀረ ኮሮናቫይረስ ዘመቻ ለኢትዮጵያ እያደረገች ያለውን ድጋፍ አድንቀዋል። ኢትዮጵያ ከቻይና ኩባንያዎች ጋር በመኾን የኮሮናቫይረስ ክትባትን በሀገር ውስጥ የማምረት ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።
የቻይናው ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው ቻይና ለኢትዮጵያ እያደረገች ያለውን የኮሮናቫይረስ ክትባት ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጸዋል። የኮሮናቫይረስ ክትባትን ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለማዘጋጀት የሚፈልጉ ኩባንያዎቿን እንደምታበረታታ አስረድተዋል።
ኹለቱ ወገኖች የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት እና የመንገድ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ የአዲስ አበባ ጅቡቲ የባቡር መስመር ዝርጋታ እና ጥገናን ጨምሮ ሌሎችም በሀገራቱ መካከል ተግባራዊ ትብብር ስለመኖሩ መገለጫዎች መኾናቸውን ጠቅሰዋል።
ሀገራቱ በባለብዙ ወገን መድረኮች የሚያደርጉትን ትብብር አጠናክሮ ለማስቀጠል ያላቸውን ቁርጠኝነት መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleቻይና በአማራ ክልል በኢንቨስትመንት ዘርፍ ያላትን ተሳትፎ አጠናክራ እንድትቀጥል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ጥሪ አቀረቡ።
Next article“አሜሪካ በአማራ ክልል የምታደርገው ሰብዓዊ ድጋፍ እና መልሶ ግንባታ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)