ቻይና በአማራ ክልል በኢንቨስትመንት ዘርፍ ያላትን ተሳትፎ አጠናክራ እንድትቀጥል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ጥሪ አቀረቡ።

176

ባሕር ዳር: መጋቢት 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ዛሬ በቢሯቸው በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛሆ ዥዩዋን ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይታቸው የቻይናው አምባሳደር ዛኦ ዥዩዋን ኢትዮጵያ ለቻይና ስትራቴጂያዊ አጋር መኾኗን ገልጸዋል፡፡ አማራ ክልል እምቅ ሀብት ያለው መኾኑን ያነሱት አምባሳደሩ የቻይና ኩባንያዎች በክልሉ መዋዕለንዋያቸውን እያፈሰሱ ስለመኾኑም ተናግረዋል፡፡ በተለይ በከተማ ልማት፣ በግንባታ፣ በግብርና እና በኢንዱስትሪ ዘርፎች የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎችን እያከናወኑ እንደኾነም ገልጸዋል፡፡
ቻይና ባሉት አማራጮች ኹሉ አብሮ ለመሥራት ቁርጠኛ መኾኗንም አረጋግጠዋል፡፡ በክልሉ የቻይና ኩባንያዎች መዋዕለንዋያቸውን እንደሚያፈስሱም አመላክተዋል።
ለዚህም የክልሉ መንግሥት አስተማማኝ ሰላምና ደኅንነት ማረጋገጥ እንዳለበት አስታውቀዋል፡፡
በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ልማት እንዲዲረጋገጥ ቻይና የበኩሏን ሚና ትወጣለች ነው ያሉት።

ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በበኩላቸው ቻይና በክልሉ የምታደርገውን ኹለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴ አድንቀዋል፡፡ በተለይ በግንባታ ዘርፉ ቻይና ጉልህ አሻራዋን እያሳረፈች እንደኾነ ገልጸዋል፡፡ ባለሀብቶች በክልሉ በልዩ ልዩ አማራጮች እንዲሠማሩም የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ነው ያሉት፡፡ የክልሉ ሕዝብ ልማት ወዳድ እንደኾነም ተናግረዋል፡፡
አምባሳደሩ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ይበልጥ በማጠናከር ቻይና በክልሉ በተለይ በኢንቨስትመንት ዘርፉ ያላትን ተሳትፎ ይበልጥ እንድታጠናክር የማድረግ ሚና እንደሚጫወቱ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በፈጸመው ወረራ በንጹሐን ዜጎች ላይ ኢሰብዓዊ ድርጊት መፈጸሙን፣ የግልና የመንግሥት ሀብት መዝረፉንና ማውደሙን አብራርተዋል፡፡
የአሸባሪ ቡድኑ ወረራ በወገን ጦር ጀግንነት ተቀልብሷል ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ።
በኢትዮጵያ ላይ የሚደረጉ ጫናዎችን ለመመከት ቻይና ከኢትዮጵያ እና ከእውነት ጎን ቆማ ላደረገችው ድጋፍና ትብብር ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
መንግሥት የደረሰውን ኹለንተናዊ ውድመት መልሶ ለመገንባት ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ መኾኑንም ተናግረዋል፡፡በመልሶ ግንባታ ሂደቱ የሚመለከታቸው እና አጋር አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ እየጠየቅን ነው ብለዋል። የቻይና መንግሥት የጀመረውን ኹለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡
ከውይይቱ መልስም በባሕር ዳር ከተማ በቻይናው ሲ ሲ ሲ ሲ ኩባንያ እየተገነባ ያለውን ግዙፍ የዓባይ ድልድይ ጎብኝተዋል፡፡
ዘጋቢ:- ደጀኔ በቀለ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየወልድያ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 220 ተማሪዎችን የፊታችን ቅዳሜ ያስመርቃል።
Next articleኢትዮጵያ እና ቻይና ስትራቴጂካዊ የትብብር አጋርነታቸውን እንደሚያጠናክሩ ገለጹ።