
መጋቢት 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 220 የጤና ሳይንስ ተማሪዎቹን የፊታችን ቅዳሜ በወልድያ ባህል አዳራሽ እንደሚያስመርቅ አስታወቀ፡፡
ተማሪዎቹ መስከረም 22/2014 ዓ.ም መመረቅ የነበረባቸው ቢኾንም የመመረቂያ ጊዜያቸው በአሸባሪው የትግራይ ቡድን ወረራ ትምህርታቸው ተስተጓጉሎ ምረቃቸውም መራዘሙን የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አስማማው ደምስ ገልጸዋል።
ተማሪዎቹ ትምህርት ሚኒስቴር ባደረገው ምደባ መሠረት የቀራቸውን ትምህርት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማጠናቀቃቸውን የገለፁት ዲኑ አሁን ምረቃቸውን በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ለማከናወን ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ መኾኑን ተናግረዋል፡፡
ኮሌጁ ከሦስት ትምህርት ቤቶችና ከአንድ ትምህርት ክፍል በመጀመሪያ ዲግሪ 202 እንዲሁም በ2ኛ ድግሪ 18፤ በድምሩ 220 ተማሪዎችን ለ5ኛ ዙር እንደሚያስመርቅ መግለጻቸውን ከዩኒቨርሲቲው የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ያሉ የ2014 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎቹን የሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርታቸውን በግቢያቸው ተከታትለው እንዲመረቁ በትናንትናው ዕለት ጥሪ አስተላልፏል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/