
መጋቢት 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት ስምንት ወራት 221 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ በበርካታ ተግዳሮቶች ውስጥ ኾኖ 221 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ነው ያስታወቀው፡፡
• ከሐምሌ እስከ የካቲት 30/ 2014 ዓ.ም 221 ቢሊዮን ነጥብ 487 ሚሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፡፡
• 240 ቢሊዮን 338 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ነበር፡፡
• 221 ቢሊዮን 487 ሚሊዮን ብር ደግሞ ሰብስቧል፡፡
• 92 ነጥብ 16 በመቶ የእቅዱን ፈጽሟል፡፡
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሰበሰበው ገቢ ከ2013 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወራት ጋር ሲነፃፀር የ30 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ጭማሪ አሳይቷል ነው የተባለው፡፡
ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወራት አንጻር 15 ነጥብ 78 በመቶ እድገት ማሳየቱንም አስታውቋል፡፡
ገቢው የተሰበሰበው ከሀገር ውስጥ ታክስ፣ ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ መኾኑም ተመላክቷል፡፡
በኢትዮጵያ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት አራት የተቋሙ ቅርንጫፎች ከሥራ ውጭ ኾነው፣ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝና መሰል ተጨማሪ ችግሮች ውስጥ ኾኖ የሰበሰበው ገቢ መኾኑም ታውቋል፡፡
ከነበረው ችግር አኳያ የተሰበሰው ገቢ ጥሩ አፈፃፀም መኾኑም ተመላክቷል፡፡ ለተመዘገበው መልካም ውጤት ምንም ዓይነት ምክንያት ሳያሳብቡ በወቅቱ ግብራቸውን አስታውቀው የሚከፈሉ ግብር ከፋዮች፣ የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣታቸው፣ አጋር አካላት እና የሕዝብ ድጋፍ ከፍተኛ መኾኑ ተገልጿል፡፡
ለተመዘገበው ውጤትና ለነበረው የጋራ ጥረት የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው ምሥጋና አቅርበዋል፡፡ በቀሪ ወራት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የተለመደው መልካም ሥራና ትብብር ቀጣይነት እንዲኖረው ሚኒስትሩ ላቀ አያሌው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/