“የአማራ ክልል ፖሊስ ሕዝባዊ ወገንተኝነቱን በማጉላት ለሥነ-ምግባር ተገዥ ኾኖ የሕዝብ ደኅንነትን ለማረጋገጥ ይሠራል” የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ

819

ደብረ ብርሃን: መጋቢት 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በሰሜን ሸዋ ዞን ከሚገኙ የፖሊስና አድማ መከላከል አመራሮችና አባላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

በውይይቱም የፖሊስ አባላትና አመራሩ ለሕዝብ በመወገን ደኅንነቱን ማስጠበቅ እንደሚገባ ተነስቷል። ውይይቱን እየመሩ የሚገኙት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ “የአማራ ክልል ፖሊስ ሕዝባዊ ወገንተኝነቱን በማጉላት ለሥነምግባር ተገዥ ኾኖ የሕዝብ ደኅንነትን ለማረጋገጥ ይሠራል” ብለዋል።

በኅልውና ዘመቻው የፖሊስ ሠራዊቱ ከሌሎች የጸጥታ ኀይሎች ጋር በመኾን ያስመዘገበው ጀብድ ከፍተኛ መኾኑ በውይይቱ ተጠቅሷል።

በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩና የኅብረተሰቡን ሰላም የሚረብሹ ሕገ ወጥ ተግባራትን በጋራ መታገል እንደሚያስፈልግም ተነስቷል።

ዘጋቢ:- ኤልያስ ፈጠነ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleትኩረት የሚሻው የተፈናቃዮች ሁኔታ።
Next articleየገቢዎች ሚኒስቴር በስምንት ወራት 221 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡