“መከላከያ ሠራዊት የተጣለበትን ሕዝባዊ ኀላፊነት በብቃት ለመፈፀም በሚያስችለው የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል” ሌተናል ጄነራል አጫሉ ሸለመ

409

መጋቢት 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የተጣለበትን ሕዝባዊ ኀላፊነት በብቃት ለመፈፀም በሚያስችለው የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የመከላከያ ሕብረት የሰው ሀብት አመራር ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄነራል አጫሉ ሸለመ ገለጹ።
የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በመሰረታዊ የዉትድርና ሙያ ያሰለጠናቸውን ምልምል የሠራዊት አባላትን አስመረቋል።
በምረቃው ሥነ-ሥርዓት የመከላከያ ሕብረት የሰው ሀብት አመራር ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አጫሉ ሸለመ
“ተመራቂዎች ወታደራዊ ስልጠናችሁን በብቃት በማጠናቀቃችሁ እና የድል አድራጊው ሠራዊት አባል በመሆችሁ እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል፡፡

ተመራቂዎቹ በማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ቆይታችው የቀሰሙትን ወታደራዊ ዕዉቀት ወደ ተግባር በመቀየር ሕዝብ እና መንግሥት የሰጧቸውን አደራ በቅንነትና በታማኝነት መወጣት ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት።
የኢፌዴሪ የመከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያን ጠላቶች እኩይ ሴራ ለማክሸፍ እንደወትሮው ኹሉ ዛሬም በተሟላ የዝግጁነት ቁመና ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ዋና አዛዥ ኮሎኔል አዲሱ ተርፋሳ ተመራቂዎች በትምህርት ቤቱ ቆይታቸው በቀጣይ የሚጠብቃቸውን ተልዕኮ ግምት ውስጥ ያስገቡ በንድፈ ሐሳብ እና በተግባር የተደገፉ ልዩ ልዩ ወታደራዊ ስልጠናዎችን እንደተከታተሉ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ይፋ ኾነ።
Next article“ቻይና በባለብዙ ወገን መድረኮች ያደረገችው ​​ድጋፍ ኢትዮጵያ በሉዓላዊነቷ እና በግዛት አንድነቷ ላይ የተደቀኑ አደጋዎችን እንድታከሽፍ አግዟል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን