የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ይፋ ኾነ።

1274

መጋቢት 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ.ር) ለጋዜጠኞች የ12ኛ ክፍል መለቀቂያ ፈተና መቁረጫ ነጥብ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።
በሁለት ዙር ለተሰጠው የመልቀቂያ ፈተና የተሰጠው የማለፊያ ነጥብ የተለያየ መሆኑ የተገለፀ ሲኾን በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማኅበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤት ይፋ ተደርጓል።
በመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 363 ለሴት 351 ሲኾን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 351 ለሴት 339 ማለፊያ ነጥብ መኾኑ ተገልጿል።
ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ኹለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 300 ሆኗል። በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 380 ኾኖ መቆረጡ ተገልጿል።
በመጀመሪያው ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 300 ኾኗል።
ለማኅበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 264፣ ለሴት 254 ሲኾን በማኅበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 254፣ ለሴት 250 ማለፊያ ነጥብ ኾኖ ተቆርጧል።
ለማኅበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ኹለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 250 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 280 እንደኾነ ተገልጿል።
በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማኅበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 250 ኾኗል።
በሁለተኛ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማኅበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤትም ይፋ ተደርጓል።
በመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 423 ለሴት 409 ሲኾን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 410 ለሴት 396 ማለፊያ ነጥብ መኾኑ ተገልጿል።
ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ኹለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 350 ኾኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 443 ኾኖ መቆረጡ ተገልጿል።
በሁለተኛ ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ350 በላይ መኾኑ ተነግሯል።
ለማኅበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 317 ፣ ለሴት 305 ሲኾን በማኅበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 305፣ ለሴት 300 ማለፊያ ነጥብ ኾኗል።
ለማኅበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ኹለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 300 እና በማኅበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለኹለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 335 እንደኾነ ተገልጿል።
በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማኅበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ 300 በላይ መኾኑም ተገለጿል።
ውጤቱ ለመጀመርያ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 እንዲሁም ለማኅበራዊ ሳይንስ ከ500 የተያዘ መኾኑን እና በኹለተኛ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 እንዲሁም ለማኅበራዊ ሳይንስ ከ600 የተያዘ መኾኑን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleʺበእነርሱ መደሰት በእነርሱ ፈገግታ፣ ይታየኛል ተስፋ፣ ይታየኛል ደስታ”
Next article“መከላከያ ሠራዊት የተጣለበትን ሕዝባዊ ኀላፊነት በብቃት ለመፈፀም በሚያስችለው የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል” ሌተናል ጄነራል አጫሉ ሸለመ