ሕገ መንግሥቱ መሻሻል ያለበት ሕዝብን ባሳተፈ፣ ሕግና ሥርዓትን በተከተለ አግባብ መኾን እንዳለበት ፓርቲያቸው እንደሚያምን ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

323

መጋቢት 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ብልጽግና ፓርቲ ሕገ መንግሥቱ ተቀዶ መጣል አለበት፣ ሕገ መንግሥቱም መነካት የለበትም የሚሉት ዋልታ ረገጥ ሐሳቦችን እንደማይቀበል የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ገልጸዋል፡፡

በብልጽግና ፓርቲ የመጀመሪያ ጉባኤ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት የፓርቲው ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ሕገ መንግሥቱ እንደ መጽሐፍ ቅዱስና እንደ ቅዱስ ቁርዓን መነካት የለበትም የሚለውን ሐሳብም አይቀበለም ብለዋል፡፡ ብልጽግና ፓርቲ ሕገ መንግሥቱም ኾነ የፓርቲው ሕገ ደንብ ከጊዜ ጋር እኛ ስናድግ ይሻሻላል ብሎ ያምናል፤ አቋማችንም ይሄው ነው ብለዋል፡፡ “እኛ ስናድግ እና እኛ ስንቀየር ለመቀየር እና ለመማር ክፍት ነን” ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፡፡

ሕገ መንግሥቱ መሻሻል ያለበት ሕዝብን ባሳተፈ፣ ሕግና ሥርዓትን በተከተለ አግባብ መኾን እንዳለበት ፓርቲያቸው እንደሚያምንም ገልጸዋል፡፡ የሚሻሻል የሕገ መንግሥት አንቀጽ ካለ ሕዝብ ይወያይበታል፣ እኛ ተሰብስበን አንወስንም ነው ያሉት፡፡ ሕጋዊ መንገድም መከተል አለብንም ብለዋል፡፡

ሕገ መንግሥት ፓርቲዎች በመጡ ቁጥር የሚያፈርሱት ከኾነ ጥፋት ነው ያሉት የፓርቲው ፕሬዚዳንት አፍርሶ መገንባት ኢትዮጵያን ጎድቷል ብለዋል፡፡

ኢህአዴግ መንግሥት ኾኖ ሲመጣ ሕገ መንግሥትንና መከላከያ ሠራዊትን እንደበተነ ያስታወሱት ዶክተር ዐቢይ አፍርሶ መገንባት ኢትዮጵያን ጎድቷል፣ የመጣው ኹሉ እያፈረሰ ስለሚሄድ እኛ ግን ያን አናደርግም ብለን ለውጥ መጥተናል ብለናል ነው ያሉት፡፡

ጠቃሚ ሐሳብ ከመጣ ለመቀበል ዝግጁ መኾናቸውንም ገልጸዋል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሕገ መንግሥት ላይ መወሰን እንደማይችሉና ሕገ መንግሥት ላይ መወሰን የሚችለው ሕዝብ መኾኑን አስታውቀዋል፡፡ ፓርቲያቸው በዚያ ውሳኔ እንደሚገዛም ተናግረዋል፡፡

የአማራ ሕዝብ በሕገ መንግሥቱ ላይ ያለው ከፍተኛ ጥያቄ ሕገ መንግሥቱ አይረባም ብቻ ሳይኾን አልተሳተፍኩም የሚል ነው ያሉት ዶክተር ዐቢይ ይህን መድገም የለብንም፣ አሳትፈን አወያይተን ሕዝቡ እንዲወስን እናደርጋለን ነው ያሉት፡፡ ሕዝብ እናሳትፋለን፣ ሕግ ተከትለን እናሻሽላለን፣ አይሻሻልም የሚል ሐሳብ የለንምም ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዐተ ቀብር ተፈጸመ፡፡
Next articleበኩር ጋዜጣ መጋቢት 05/2014 ዓ.ም ዕትም