
መጋቢት 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አራተኛው የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዐተ ቀብር በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡
ብፁዕነታቸው በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በመዘዋወር ዕውቀትን በመቅሰም አገልግሎት ሰጥተዋል። በሕይወት ዘመናቸው የቤተክርስቲያንን ተልዕኮና አገልግሎት ለመፈፀም ሲፋጠኑ ኖረዋል።
የብፁዕነታቸው ሥርዐተ ቀብር በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሊቃነ ጳጳሳት፣ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት እና የተለያዩ ሀገራት የሃይማኖት አባቶች በተገኙበት ተፈፅሟል።
ዘጋቢ፡- አየለ መስፍን – ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J