
ባሕር ዳር: መጋቢት 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ አየር መንገድ የባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ አየር ማረፊያ ሥራ አስኪያጅ ተስፋየ ቀለሙ ለአሚኮ እንደገለጹት ከመጋቢት 2/2014 ዓ.ም ምሽት ጀምሮ በተከሰተ አቧራ መሰል ጭጋግ ምክንያት መጋቢት 3/2014 ዓ.ም ሊደረጉ የነበሩ 11 በረራዎች ተሰርዘዋል።
እንዲህ አይነቱ ክስተት ባለፈው ዓመትም በተመሳሳይ ወር ተከስቶ እንደነበር አስታውሰዋል።
የአየር ሁኔታው እንደተስተካከለ የበረራ አገልግሎቱ እንደሚቀጥልም ነው አቶ ተስፋየ የተናገሩት።
ክስተቱ ዛሬ 11:00 ላይ በጎንደርም ያጋጠመ ቢኾንም የአየር ሁኔታው በመስተካከሉ አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝ ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ምስጋናው ብርሃኔ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/