መጋቢት 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሽኝት መርኃ ግብሩ ባደረጉት ንግግር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በመከራ ቀንም ቢሆን የማትጠገብ የራሷ ታሪክ፣ ባሕል፣ ዜማና ማንነት ያላት መኾኗን ለማሳዬት ምክንያት ስለሆኑን ማመስገን ይገባል ብለዋል፡፡

ብፁዕ አባታችን እንደ ጥሩ አባት ሩጫቸውን ጨርሰው ወደሚወዱትና እድሜ ልካቸውን ወደ አገለገሉት አባታቸው መሄዳቸውንም ተናግረዋል፡፡

ምንም እንኳን አርምሞን መርጠው ከመናገር ቢታቀቡም በዋሽንግተን ዲሲ በነበራቸው የመጀመሪያ ግንኙነት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ በነበረው ወሳኝ ጊዜ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ሲወስኑ ድንቅ ንግግር ማድረጋቸውን አስታውሰዋል፡፡

ሀገር ውስጥ በነበራቸው ቆይታ አልፎ አልፎ የመጎብኘት እድል አግኝቻለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእጅጉ በጸሎት ያግዟቸው እንደነበር፣ ምክርም ይሰጧቸው እንደነበር አብራርተዋል፡፡

ሀገሪቱ የከፋ ችግር በገጠማት ጊዜም ቢሮ ድረስ በመሄድ ሀሳባቸውን በጽሑፍ ይገልጹላቸው እንደነበር አስታውሰው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ለእኔም የመንፈስና የጸሎት አባቴ ነበሩ ብለዋል፡፡

አባቴን እንዳጣሁ ይሰማኛል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥልቅ ሐዘንም እንደተሰማቸው ተናግረዋል፡፡

ብፁዕ አባታችን አብዝተው የሚወዷትን ቤተክርስቲያናቸውን እድሜ ዘመናቸውን ሙሉ አገልግለዋል፡፡ ለእኛም በብዙ አስተምረውናል ብለዋል፡፡

ዘጋቢ:–ደጀኔ በቀለ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የሚታየውን ሕገወጥነት ለመቆጣጠርና በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል ከመላው የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን እየተሠራ ይገኛል” የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Next articleአሸባሪው የትህነግ ቡድን በአማራ ክልል በወረራ ይዟቸው በነበሩ ቦታዎች የአዕምሮ ሕሙማንን ሳይቀር መግደሉን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ይፋ አድርጓል።