“የሚታየውን ሕገወጥነት ለመቆጣጠርና በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል ከመላው የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን እየተሠራ ይገኛል” የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

193

ባሕር ዳር: መጋቢት 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚታየውን ሕገወጥነት ለመቆጣጠርና በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል ከክልሉና ከመላው የጸጥታ አካላት ጋር እየተሠራ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።

በጉዳዩ ላይም የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የሰጠው መግለጫ ቀጥሎ ቀርቧል።

ፅንፈኝነት ሰላምንም ሆነ ፍትህን እዉን ሊያደርግ አይችልም!!!

ሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ አይሲድ ቀበሌ እጅግ አሰቃቂ እና ከሰብዓዊነት ያፈነገጠ ድርጊት ተፈፅሟል:: በማኅበራዊ ትስስር ገፆች በተንቀሳቃሽ ምስል ሲዘዋወር በቆየው እጅግ አሰቃቂ ድርጊት ንፁሃን ዜጎች በእሳት ተቃጥለው እንዲሞቱ ተደርጓል።

ይህ ድርጊት ከኢትዮጵያዊነት ባህል፣ እሴትና ከማንኛውም የሰብዓዊነት እሳቤ ያፈነገጠና እጅግ አሰቃቂ ወንጀል ነው።

ይህ እኩይ ድርጊት መጠፋፋትን ያፈጥን ካልሆነ በቀር ሰላምንም ሆነ ፍትሕን እዉን ሊያደርግ አይችልም:: በመሆኑም ሊኮነንና ሊወገዝ ይገባል:: መነሻቸውም ሆነ ማንነታቸዉ ምንም ይሁን ምን መንግሥት ይህን አይነት ፍፁም ከሰብዓዊነት የራቀና ጭካኔ የተሞላበትን ድርጊት የፈፀሙ አካላትን አጣርቶ ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚታየውን ሕገወጥነት ለመቆጣጠርና በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከልም ከክልሉና ከመላው የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን እየተሠራ ይገኛል።

የንፁሃን ዜጎችን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ አካላትን መንግሥት ከዚህ በኋላ አይታገስም። ስለዚህ እነዚህ በወንጀል ሥራ ላይ የተሰማሩና የዜጎችን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥሉ አካላት ከወዲሁ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግሥት በጥብቅ ያሳስባል።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ወደ ሕዝባችን የቀረብን፣ የኑሮ ውድነትን የምንፈታ የምንመራ ብቻ ሳንኾን የምናገለግል እንድንኾን አደራ እላለሁ” የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next article“ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ለእኔም የመንፈስና የጸሎት አባቴ ነበሩ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ