“ወደ ሕዝባችን የቀረብን፣ የኑሮ ውድነትን የምንፈታ የምንመራ ብቻ ሳንኾን የምናገለግል እንድንኾን አደራ እላለሁ” የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

213

መጋቢት 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ብልጽግና ፓርቲ ከፈተና ወደ ልዕልና በሚል መሪ ሐሳብ የመጀመሪያውን ጉባኤ በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው፡፡

በጉባኤው ላይ ንግግር ደረጉት የፓርቲው ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ብልጽግና በሕዝብ ግፊት በለውጥ ፍላጎት ተወልዷል ነው ያሉት፡፡ ብልጽግና በኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን በአፍሪካም ግዙፍ ፓርቲ ነውም ብለዋል፡፡ ፓርቲው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አባላት እንዳሉት ገልጸዋል፡፡

ብልጽግና በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በርካታ አባል ያለው መኾኑን አንስተዋል፡፡

ፓርቲው ሀገር በቀልን ዕውቀትና መርህ መነሻ ያደረገ ስለመኾኑም ጠቅሰዋል፡፡

ፓርቲው ከኹሉም አካባቢ በቂ ውክልና ያለው ኢትዮጵያዊ ፓርቲ ነውም ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያን መስሎ ኢትዮጵያን ለማበልጸግ የመጣ ስለመኾኑ ገልጸዋል፡፡

ፓርቲው አጋርና ዋና የሚባለውን ከፋፋይ ግንብ ያፈረሰ፣ የቀደመውን ኹሉ ያልናደ ነውም ብለዋል፡፡

የሕዝብን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የፈቀደ፣ በሲዳማና በምዕራብ ኢትዮጵያ ያረጋገጠ መኾኑን ተናግረዋል፡፡ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያካሄደ ስለመኾኑም አንስተዋል፡፡ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ካቢኔ ያቀፈና በአካታችነትም የሚያምን መኾኑንም ገልጸዋል፡፡

ፈተና ባለበት ኹሉ ድል አለ ያሉት ዶክተር ዐቢይ በማንኛውም ሰዓት የሚገጥመንን ፈተና ወደ ድል የሚቀየር ነውም ብለዋል፡፡

በአንደኛው ጉባኤ ብልጽግናን አሸናፊ የሚያደርግ የሚያሸንፈውንና የሚገዳደረውን ፈተና የሚረታ ሐሳብ፣ ጉልበትና አንድነት የሚገኝበት መኾኑንም ገልጸዋል፡፡

ከፈተና ወደ ልዕልና ሲባልም ፈተናዎችን ኹሉ አልፎ ከፍ ማለት ነውም ብለዋል፡፡

ዓላማቸው ጠንካራ ፓርቲና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት መገንባት መኾኑንም አስታውቀዋል፡፡

ፓርቲው ሌብነትን እንሚታገልም ገልጸዋል፡፡

የገጠሙንን ፈተናዎች በድል ለመሻገር በጉልበት ብቻ ሳይኾን በስሌት እንሄዳለንም ነው ያሉት፡፡

ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚያጠናክር ኹሉም ተከብሮ የሚኖርበት ኢትዮጵያን ማዬት ሕልማቸውና ዓላማቸው መኾኑንም አንስተዋል፡፡

ፓርቲው በፈተና ውስጥ ሐሳብ እያፈለቀ ወደ አሸናፊነት የሚሄድ ስለመኾኑም አንስተዋል፡፡ የሚታሰበውን ብልጽግና ለማሳካት ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር መሥራት እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

በሀገራዊ ምክክር መድረኩ ኢትዮጵያን የሚያጸና ሐሳብ እንዲወለድ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡም አሳስበዋል፡፡

“ወደ ሕዝባችን የቀረብን፣ የኑሮ ውድነትን የምንፈታ የምንመራ ብቻ ሳንኾን የምናገለግል እንድንኾን አደራ እላለሁ” ብለዋል፡፡

ኹሉም ለሰላምና ለአንድነት በጋራ እንዲቆምም ጠይቀዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየ4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የቀብር ሥነ ሥርዓትን አስመልክቶ ቤተክርስቲያኗ መግለጫ ሰጥታለች፡፡
Next article“የሚታየውን ሕገወጥነት ለመቆጣጠርና በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል ከመላው የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን እየተሠራ ይገኛል” የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት