
ባሕር ዳር: መጋቢት 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የ4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሽኝት መርኃግብር ነገ እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡
መጋቢት 3/2014 ዓ.ም የሽኝት ሥነ ሥርዓት ሀሌሉያ ሆስፒታል ከ3 ሰዓት ጀምሮ ተነስቶ ወደ መስቀል አደባባይ በክብር እንደሚያመራ መግለጫውን የሰጡት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ተናግረዋል፡፡
ብፁዕነታቸው እንዳሉት በሽኝት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ሊቀነ ጳጳሳት፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ የመንግሥት ባለስልጣናት እና የእምነቱ ተከታዮች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በመስቀል አደባባይ የሽኝት ፕሮግራም ላይም የሚተላለፉ መንፈሳዊ መልእክቶች ይኖራል ነው የተባለው፡፡
ሥነ ሥርዓቱ እንደተጠናቀቀ ከመስቀል አደባባይም ወደ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የቅዱስነታቸው ሥርዓተ ቀብር በክብር ወደሚከናወንበት ጉዞ ይደረጋል፡፡
እሁድ መጋቢት 4/2014 ዓ.ም በሚደረገው የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይም ሊቃነ ጻጳሳት፣ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ አምባሳደሮች እና ከውጭ የሚመጡ እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
ዘጋቢ፡-ራሄል ደምሰው-ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/