
መጋቢት 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ብልጽግና ፓርቲ የመጀመሪያ ጉባኤውን በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው፡፡ጉባኤው ከፈተና ወደ ልዕልና በሚል መሪ ሐሳብ ነው የሚካሄው፡፡ በጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ፓርቲው የኢትዮጵያን ሕዝብ የሰላም፣ ፍትሕ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ፍላጎት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ወሳኝ የኾኑትን የወንድማማችነትና የእህታማማችነት እሴትን ለማጎልበት የሚታገል ነው ብለዋል፡፡
የዴሞክራሲን ባሕልን ለማጎልበት የሚታገል ኹሉንም ኢትዮጵያውያን ያለ ልዩነት ያቀፈ እውነተኛ ሕብረ ብሔራዊ ፓርቲ ነውም ብለዋል፡፡
ፓርቲው በለውጥ እንደተወለደ የተናገሩት አቶ አደም ብዙ ፈተናዎች ቢገጥሙትም ሕዝብን እያሳተፈ ችግሮቹን እየፈታ የመጣ መኾኑንም አንስተዋል፡፡ ችግሮቹን ወደ እድል እየለወጠ፣ የጎደለውን እየሞላ የመጣ ነውም ብለዋል፡፡
ለዛሬና ለነገ ትውልድ ዘላቂ ጥቅምና መብት የሚተጋ መፍትሔ ተኮር የለውጥና የቀጣይነት ፓርቲ መኾኑንም ገልጸዋል፡፡
ፓርቲው በኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰጠውን እድልና የተጣለበትን አደራ በብቃት ለመወጣት የውስጠ ፓርቲ ጥንካሬና ጥራትን የሚያረጋግጥ መኾኑንም አንስተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጠላቶች የከፈቱት ዘርፈ ብዙ ጦርነት በታቀደው ልክ እንዳይሠራ እንቅፋት ሲኾንበት እንደቆዬም ገልጸዋል፡፡ በተጀመረው ሰፊ የማጥራት ሥራ በርካታ የማስተካካያ እርምጃዎች መወሰዳቸውንም አንስተዋል፡፡ ተጨባጭ ለውጦች መመዝገባቸውንም ገልጸዋል፡፡
የተጀመረው የፓርቲውን መሪዎችና አባላት ጥራት የሚያሳድጉ ውሳኔዎች ይወሰናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አስታውቀዋል፡፡
በውጭና በውስጥ ጠላት እኩይ እንቅስቃሴ የተደቀነውን የኅልውና አደጋ በወሳኝ መልኩ በመቀልበስ የሚደረግ ጉባኤ መኾኑን ገልጸዋል፡፡ የሚካሄደው ጉባኤም ባለፉት የለውጥ ዓመታት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና የቀጣይ ኹለንተናዊ ብልጽግና አቅጣጫዎች ላይ በጥልቀት በመምከር ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅም አስታውቀዋል፡፡
ጉባኤው የአመለካከትና የተግባር አንድነት በማምጣት ፓርቲውን በአመራር፣ በአደረጃጀትና በአሠራር በማጠናከርና በማጥራት የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ በማጽናት ረገድ ሚናው ከፍ ያለ ነውም ብለዋል አቶ አደም ፋራህ፡፡
ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/