ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የተሳተፉበት ‘ኤችአር 6600’ ረቂቅ ሕግን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ።

189

መጋቢት 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የተሳተፉበት ‘ኤችአር 6600’ ረቂቅ ሕግን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በአሜሪካ ኒውጀርሲ ግዛት ዛሬ ተካሄደ፡፡
ሰልፉ የተካሄደው ሕጉን ባረቀቁት የኒው ጀርሲ የኮንግረስ አባል ቲም ማሊኖውስኪ የሚሰሩበት ቢሮ ፊት ለፊት ሲኾን እሳቸውንና ሕጉን የሚቃወሙ መልዕክቶች በሰልፉ ላይ መተላለፉን ኢዜአ ከሰልፉ አስተባባሪዎች ያገኘው መረጃ ያመላክታል።
የዳያስፖራው ተወካዮች ሕጉን በአሜሪካ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት እንደሚቃወሙትና አፍራሽ ከኾነ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ የሚያሳስብ ደብዳቤ ለኮንግረስ አባሉ ተወካዮች ሰጥተዋል።
ቶም ማሊኖውስኪ ያረቀቁት ሕግ ለረጅም ጊዜ የቆየውን የኢትዮጵያና አሜሪካ ግንኙነት የሚጎዳና የሁለቱን ሀገራት የማይጠቅም እንዲሁም በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድር መኾኑን ለተወካዮቻቸው የማስረዳት ሥራ መከናወኑ ተገልጿል።

“ቶም ማሊኖውስኪ ሽብርተኞችን መርዳት ያቁሙ ‘ኤችአር 6600’ ኢትዮጵያን የሚጎዳ ነው” የሚል መልዕክትም ተላልፏል።
ረቂቅ ሕጉ ኤርትራንም የሚመለከት በመኾኑ በሰልፉ ላይ በአሜሪካ ከሚገኙት የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች በተጨማሪ ኤርትራውያንም ተሳትፈውበታል።
በቀጣይ በአሜሪካ ትላልቅ ከተሞች ‘ኤችአር 6600’ ረቂቅ ሕግን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፎች ለማካሄድ መታሰቡ ተነግሯል።

ረቂቅ ሕጉን የሚቃወሙ እንዲሁም በአሜሪካ ኮንግረስ ለውይይት ቀርቦ ውሳኔ እንዳይሰጥበት ለማድረግ ዘመቻዎች እየተካሄዱ እንደሚገኙ ተመልክቷል።
የ‘ኤችአር 6600’ ረቂቅ ሕግን በመቃወም በአሜሪካ ኒውጀርሲ ግዛት የተካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ ተስፋ ለኢትዮጵያ ከ’አሜሪካን ኢትዮጵያን ፐብሊክ አፌርስ ኮሚቴ’(ኤፓክ)፣ ኤርትራ አሜሪካውያን ብሔራዊ ምክር ቤትና ሰላምና አንድነት የዋሺንግተን ዲሲ ግብረ ኃይል ጋር በመተባባር ያዘጋጀው እንደኾነ ተገልጿል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleʺዓለምን ናቋት በዝምታም ቀጧት”
Next article“መረጃ ያላሟላ ደንበኛ የባንኩን አገልግሎት አያገኝም በሚል የሚሰራጨው መረጃ መሰረተ ቢስ ነው” ንግድ ባንክ