የብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ የቅድመ ጉባኤ መድረክ ተጠናቀቀ፡፡

224

መጋቢት 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ለሦስት ቀናት በአዳማ ከተማ ሲካሄደው የነበረው የብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ጉባዔ የቅድመ ጉባኤ መድረክ ዛሬ ተጠናቋል፡፡

በማጠቃለያ መድረኩ ተገኝተው ማብራሪያ የሰጡት የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ደመቀ መኮንን “ከዚህ ቀደም በሀገራችን የሠራንውን የማፍረስ፣ አንድ ከሚያደርጉትን ይልቅ በሚያለያዩን ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተደርቶ መሥራት እንዲሁም ገቢራዊነት መጓደልና ግለሰቦች ከሀገር በላይ የኾኑበት ሁኔታዎች ይስተዋሉ ነበር” ብለዋል፡፡ ብልጽግና እነዚህን ችግሮች በሚፈታ መልኩ እየተጓዘ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

ባለፉት ሦስት ዓመታት በበርካታ ተግዳሮቶች ውስጥም ኾነን የሀገራችንን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ስኬቶችን አስመዝገበናል ያሉት አቶ ደመቀ ፈተናውን በዘላቂነት ለመሻገርና ኹለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ አንድነታችንን ማጠናከር አለብን ነው ያሉት፡፡

የፓርቲው አመራርና አባላት በጥብቅ ዲሲፕሊን መመራት እንዳለባቸውም ገልፀዋል፡፡ በትስስርና እውቅና መሥራት ብሎም ብልሹ አሠራሮች ለፓርቲው ጠንቅ መኾናቸውን ጠቅሰው ተግባሮችን ስንፈጽም በፓርቲው ሕግና ደንብ እንዲሁም እሴቶችና መርሆዎች ተገዝተን መሆን አለበት ብለዋል፡፡ ፓርቲው በቀጣይም ጥራት ላይ የተመሠረተ የአባላት ብዛት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ አስታውቀዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ አደም ፋራህ በበኩላቸው ከሥርዓትና ከተልዕኮ አፈፃፀም -ጋር የሚያያዙ ችግሮችን መፍትሔ በመስጠት እንዲሁም ውስጣዊ አንድነትን በማጠናከር የፓርቲውን የአጭር ጊዜ እቅዶችና የረጅም ጊዜ ራዕይ ማሳካት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ አመራሩና መላ አባላቱ ጽንፈኛ ብሔርተኝነትን አምርረው እንዲታገሉም ማሳሰባቸውን ከብልጽግና ፓርቲ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“በሀገር ግንባታው ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎች እና ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች ከጉባኤው አጀንዳዎች መካከል ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጣቸው ናቸው” ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ
Next articleʺዓለምን ናቋት በዝምታም ቀጧት”