
አዲስ አበባ: መጋቢት 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የብልጽግና ፓርቲ የመጀመሪያውን ጉባኤ ከመጋቢት 2 -4/2014 ዓ.ም ያካሂዳል።በጉባኤው 2 ሺህ ሰዎች ይሳተፋሉ። የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን፣ ወጣቶች እና ታዛቢዎች ከተሳታፊዎች መካከል ናቸው።
መጋቢት 3 እና 4/2014 ዓ.ም ፓርቲው በዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ይመክራል።
በ3 ዓመት ጊዜ ውስጥ ያከናዎናቸውን ተግባራት ስኬቶች፣ ተግዳሮቶች እና ፈተናዎች ይብራራሉ።
የተለያዩ ሐሳቦች ይንጸባረቃሉ፣ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ፣ የቀጣይ አቅጣጫዎች ይሰጣሉ ነው የተባለው።
ፓርቲው አመራሮቹን ይመርጣል።
ፓርቲውን የአስተዳደር እና የተግባር አንድነት የሚጎናፀፍበት፣ በአደረጃጀት እና አሠራር ራሡን የሚያጎለብትበት ሂደቶችን የሚያሳይበት ጉባኤ እንደሚኾንም ተገልጿል።
በሀገር ግንባታው ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎች እና ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች ከጉባኤው አጀንዳዎች መካከል ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጣቸው እንደኾነ የፓርቲው የሕዝብ እና የዓለምአቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ በሰጡት መግለጫ ጠቅሰዋል።
ዘጋቢ:- በለጠ ታረቀኝ – ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/