የኢትዮጵያ-እስራኤል ፓርላማ ወዳጅነት ሕብረት ለኢትዮጵያ ስለሚደረግ ድጋፍ ምክክር አደረገ፡፡

217

መጋቢት 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ-እስራኤል ፓርላማ ወዳጅነት ሕብረት በእስራኤል ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ምክክር አድርጓል። ምክክሩ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሚውል ድጋፍ ማሰባሰብ ላይ ያተኮረ ነው።

የእስራኤል ፓርላማ አባል እና የኢትዮጵያ-እስራኤል ፓርላማዊ ወዳጅነት ሕብረት ሊቀመንበር ጋዲ ይቫርካን ኢትዮጵያ ከምንጊዜውም በላይ የወገኖቿን ድጋፍና እርዳታ የሚያስፈልጋት ወቅት ላይ እንደምትገኝ ገልጸው ይህንንም ለመፈጸም የኹሉም ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ረታ ዓለሙ በአሸባሪ ቡድኖች የተፈጸመውን ግፍ፣ የጤና ተቋማት፣ ትምህርት ቤት እንዲሁም ከፍተኛ የመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ የደረሰውን ውድመት እንዲሁም በድርቅ ምክንያት የተከሰተ ችግር እና የሚያስፈልግ ሰብዓዊና ቁሳዊ ድጋፎችን በሚመለከት ገለጻ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም፣ የወደሙ ተቋማት ለመገንባት ፣ የሰብዓዊ እርዳታ እና ቁሳዊ ድጋፎችን ለማድረስ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ቢኾንም፣ ካለው ጫና እና ከችግሩ ስፋት የተነሳ የወዳጆችን እርዳታ ማግኘት አስፈላጊ እንደኾነ ገልጸዋል፡፡ የሚደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ አፋጣኝ ለኾን እንደሚገባውም አስገንዝበዋል፡፡

በእስራኤል የሚገኙ የሕክምና ተቋማት እና መንግሥታዊ ተቋማት ግብረ-ሰናይ ድርጅቶችን በማስተባበር ለኢትዮጵያ የሕክምና፣ የትምህርት መገልገያዎች እንዲሁም የምግብ እርዳታ ለመላክ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በውይይቱ የእስራኤል ፓርላማ አባላት፣ የእስራኤል መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ባለሐብቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እንዲሁም መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መሳተፋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article‹‹ወቅታዊውን የዋግ ሕዝብ የከፋ ችግር መመልከት እና ምላሽ መስጠት ከኢትዮጵያዊነት በላይ ሰብዓዊነትም ነው!››
Next articleዜና መጽሔት ባሕር ዳር: መጋቢት 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ)