“ጦርነት ያልገደበው ለሙያዊ ቃል-ኪዳን የታመነ አገልግሎት”

266

ከሚሴ: የካቲት 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አዋላጅ ነርስ በቀለ ይልማ ይባላል። በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር በደዋ ጨፋ ወረዳ ወለዲ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ነው የሚሠራው።

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን እና ተላላኪው ኦነግ ሸኔ ወለዲ ከተማንና አካባቢውን ወርረው በነበረበት ጊዜ ጦርነቱ ሳይበግረው ሙያዊ ኀላፊነቱን ሲወጣ ቆይቷል።

ኢንጅነር የመሆን ህልም እንደነበረው የሚናገረው የጤና ባለሙያው በቀለ በአንድ አጋጣሚ በተመለከተው የጤና ባለሙያዎች እጥረት እና የኅብረተሰቡ ችግር ሀሳቡን እንዲቀይር እንዳደረገው ለአሚኮ ገልጿል፡፡

እናቶችን ለማገልገል ከፍተኛ ፍላጎት የነበረው የጤና ባለሙያው ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በአዋላጅ ነርስነት ተመርቋል፡፡ በተመረቀበት የሙያ ዘርፍ ሳይማር ያስተማረውን ወገኑን በሃይማኖት፣ በዘርና በቋንቋ ሳይለይ በየትኛውም ቦታና በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ኾኖ ለማገልገል ቃል የገባው አዋላጅ ነርስ በቀለ በገባው ቃል መሰረት በነበረው ጦርነት ውስጥ ኾኖ ሙያዊ ኀላፊነቱን መወጣቱን አስረድቷል።

በወቅቱ ባደረገው ጥረት 22 እናቶችን በማዋለድ ኅብረተሰቡን ማገልገሉንም ገልጿል፡፡ በወሊድ ጊዜ ደም መፍሰስን ለማስቆም የሚያገለግሉ እንደ ኦክስቶሲን፣ ኢንሱሊንና ሌሎችንም በማቀዝቀዣ ውስጥ መኾን ያለባቸውን መድኃኒቶች በአሸዋ በመሸፈን እንዲቀዘቅዙ በማድረግ እናቶች በወሊድ ምክንያት በህክምና እጦት እንዳይሞቱ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግም ቆይቷል።

አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በከተማው የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና ጤና ጣቢያውን በከፍተኛ ደረጃ በማውደሙ አሁን ድረስ ኅብረተሰቡ ችግር ውስጥ መኾኑንም ተናግሯል።

አሚኮ ያነጋገራቸው የወለዲ ከተማ ነዋሪ ጀማነሽ ሙሃባ እና ፋጡማ መሐመድ በአስቸጋሪው ጊዜ የጤና ባለሙያው እንዳገዛቸው ተናግረዋል።

ዘጋቢ፡- ሥነ ጊዮርጊስ ከበደ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com

Previous article“ነፃነታችን የአማራነታችን ፋና ወጊ ነው” የሑመራ ከተማ ሴቶች
Next articleምርታማነት በማሳደግ ረገድ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚያስፈልግ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ አማንይሁን ረዳ ገለጹ።