“ነፃነታችን የአማራነታችን ፋና ወጊ ነው” የሑመራ ከተማ ሴቶች

217

ሑመራ: የካቲት 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የክት ልብሳቸውን እንዳይለብሱ፣ በባህላቸው እንዳይጨፍሩ፣ በቋንቋቸው እንዳይናገሩ፣ ወግና ትውፊታቸውን ለልጆቻቸው እንዳያስተምሩ፣ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን ሴቶች ከፍተኛ ጫና ይደርስባቸው ነበር።

ይህ ጭቆናና ግፍ ያልበገራቸው የወልቃይት ጠገዴ ሴቶች ነፃነታቸውን ለመጎናፀፍ ከፍተኛ ተጋድሎ አድርገዋል።

የነፃነትን አየር መተንፈስ ከጀመሩ በኋላ ባህላቸውን አጉልተው እያሳዩ ነው። በኢትዮጵያ ለ46ኛ እንዲሁም በአማራ ክልል ለ27ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን የሴቶች ቀንንም የክት ልብሳቸውን ለብሰው በራሳቸው ቋንቋና ባህል በፖናል ውይይት አክብረዋል።

በፖናል ውይይቱ ላይ የሑመራ ከተማ ከንቲባ ሙሃመድ ኑሩ ሴቶች በህልውና ዘመቻው ያሳያችሁትን ቁርጠኝነት አሁንም በኹሉም ዘርፍ ተሳታፊ በመኾን አጠናክራችሁ ልትቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

ኢትዮጵያ የሴቶችን እኩልነትና የመሪነታቸውን ጥበብ በዓድዋ ጦርነት ለዓለም ያስመሰከረች ሀገር እንደሆነች የሑመራ ከተማ የሴቶችና ወጣቶች ማኅበራዊ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሺፋና ዋኘው ገልጸዋል። የእናቶቻችንን የጥንካሬ ታሪክ ልናስቀጥልም ይገባል ብለዋል።

ባህልና ወጋችንን ለማጥፋት በርካታ ሴራ ተሰርቶብናል ነፃነታችንን ተጠቅመን አማራዊ ቱባ ባህላችንን ለዓለም ልናሳውቅ ይገባል ነው ያሉት።

ነፃነታችን የአማራነታችን ፋና ወጊ ነው ያሉት የውይይቱ ተሳታፊ ሴቶች በአሸባሪው ትህነግ አገዛዝ ዘመን በተለያዩ በዓላትና በሴቶች ቀን የክት ልብሳቸውን እንዳይለብሱ፣ በቋንቋቸው እንዳይናገሩ፣ በሴቶች ተሳትፎ ውጤታማ እንዳይኾኑ ከፍተኛ ጫና ይደርስባቸው እንደነበር ተናግረዋል።

በውይይቱም አማራዊ ቱባ ባህላቸውን ይበልጥ ለማሳየት እንደሚሠሩ የተናገሩት ነዋሪዎቹ በህልውና ዘመቻው ያሳዩትን አንድነት በማጠናከር ነፃነታቸውን አስጠብቀው ለመዝለቅ በኬላ ፍተሻና በልማት በቁርጠኝነት ተሳታፊ እንደሚሆኑ ቃል ገብተዋል።

ዘጋቢ:–ያየህ ፈንቴ –ከሑመራ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየቀድሞው የሰሜን ሸዋ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ሥርዓተ ቀብር የፊታችን ሐሙስ እንደሚከናወን የሰሜን ሸዋ ሀገረስብከት አስታወቀ።
Next article“ጦርነት ያልገደበው ለሙያዊ ቃል-ኪዳን የታመነ አገልግሎት”