የቀድሞው የሰሜን ሸዋ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ሥርዓተ ቀብር የፊታችን ሐሙስ እንደሚከናወን የሰሜን ሸዋ ሀገረስብከት አስታወቀ።

294

ደብረ ብርሃን: የካቲት 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሐዲስ ነቅዐ ጥበብ አባቡ በሰጡት መግለጫ የብፁዕነታቸው የቀብር ሥነ ሥርዓት የፊታችን ሐሙስ መጋቢት 1/2014 ዓ.ም ይከናወናል ብለዋል። የቀብር ሥርዓታቸውም በደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ነው የገለጹት።

የአረጋዊው ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የቀብር ሥርዓትም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብፁዓን አባቶች በተገኙበት ይፈፀማል ሲል ሀገረስብከቱ በመግለጫው አመላክቷል።

ሀገረ ስብከቱ ብፁዕነታቸው ከዚህ ዓለም ድካም በማረፋቸው የተሰማውን መሪር ሐዘን ገልጿል።

ዘጋቢ፡- ኤልያስ ፈጠነ-ከደብረብርሃን

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

Previous articleፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በኅልውና ዘመቻው ከፍተኛ ተጋድሎ ላደረጉ ሴት የሠራዊት አባላት እውቅና ሰጡ።
Next article“ነፃነታችን የአማራነታችን ፋና ወጊ ነው” የሑመራ ከተማ ሴቶች